የአዉሮጳ ሕብረት ድጋፍ፤ ኬንያ
ማክሰኞ፣ ጥር 15 2010ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት ለኬንያ መንግሥት ይሰጠዉ የነበረዉን የ35 ሚሊዮን ዩሮ የተፈጥሮ ሐብት ማስጠበቂያ ርዳታ አቋረጠ።ርዳታዉ የኬንያ መንግሥት የዉኃ እና የከባቢ ዓየርን ለመጠበቅ ለነደፈዉ ዕቅድ የሚዉል ነበር።ሕብረቱ ድጋፉን ያቋረጠዉ የኬንያ መንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች በደን በተሸፈኑ አካባቢዎች በሚኖሩ ጎሳ አባላት ላይ ይፈፅሙታል የተባለዉን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመቃወም ነዉ።የኬንያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ የሚያደርሰዉን ግድያና በደል እንዲያቆም የተለያዩ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ሲያሳስቡ ነበር።
ሐብታሙ ስዩም
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ