የአንጋፋዎቹ አመራሮች ሞት እና ህወሓት
ሐሙስ፣ ጥር 6 2013ማስታወቂያ
የህወሓት መሥራች የሆኑት የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የፌድራል ጉዳዮች ምኒስትር በአንድ ወቅት ደግሞ የጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የነበሩት አቶ አባይ ጸሀዬ መገደላቸውን የኢትዮጵያ ጦር ትናንት አስታውቋል። ቀደም ብሎ ሌላው ጉምቱ የህወሓት ፖለቲከኛ አቶ ዘርዓይ አስገዶም መገደላቸው ተገልጾ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ስብሐት ነጋ እና አቶ አባይ ወልዱን የመሳሰሉ ፖለቲከኞችም ታስረዋል። ይኸ በህወሓት ላይ ምን ያክል ጉዳት ያስከትላል? ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት የፖለቲካ ተንታኙ ቻላቸው ታደሰን አነጋግሬዋለሁ።
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሠ