1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንቶኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝትና አንደምታዉ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 5 2015

"ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን፣በጸጥታውም አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለመገምገም እና የትግራዩን ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያውያን በንፁሃን ዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለው የጅምላ ጥቃትና ጭፍጨፋ ዘርን መሰረት ያደረገ ጨፍጨፋ፣ ለማስቆም መንግስት ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ይመስለኛል።"

https://p.dw.com/p/4OevR
Indien | G20 Antony Blinken
ምስል Olivier Douliery/AP Photo/picture alliance

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት


የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ ከዛሬ መጋቢት አምስት እስከ መጋቢት ስምንት ቀን 2015 ድረስ  ወደ ኢትዮጵያና ኒጀር እንደሚያቀኑ መስሪያ ቤታቸው  ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

አንቶኒ ብሊንከን፣  በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ጉብኝት በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለማስቆም የተደረሰው የሰላም ስምምነት አተገባበር እና የሽግግር ፍትህ ጉዳይ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

 የኢትዮጵያንና የአሜሪካን ፖለቲካዊ ጉዳዮች በቅርበት የሚከታተሉት፣ልጅ ነቢያት አክሊሉ እንደሚሉት፣ብሊንከን በዚህ ጉብኝታቸው፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የተደረሰዉ ስምምነት መሬት ላይ ወርዶ በትክክል ተፈጻሚ የመሆን ያለመሆኑን ጉዳይ እንደሚገመግሙ ይጠበቃል።

"በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ውል ባግባቡ መሬት በአግባቡ መሬት ላይ ወርዶ ተግባራዊ ስለመሆን አለመሆኑ ያንን ለማረጋገጥና በመንግስትና መሬት ላይ ባሉትም የፖለቲካ ኃይላት ተጽዕኖ ለመፍጠር እና ሰላምና መረጋጋት እንዲመለስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ የሄዱ ይመስለኛል።"

Kenia Nairobi | Abkommen zwischen äthiopischer Regierung und Tigray Rebellen | Birhanu Jula und Tadesse Werede Tesfay
የፕሪቶርያዉ ስምምነት ምስል Thomas Mukoya/REUTERS

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ከዚህ ቀዳም ባወጡት መግለጫ፣ ከሰሜን ኢትዮጵያ በተጨማሪ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል ያለው የጸጥታ ችግርና የፖለቲካ አለመረጋጋት ስጋት እየፈጠረ መሆኑን አንስተው ነበር።

በመሆኑም በዚህ ጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሚያደርጉት ውይይት፣ የአገሪቱን አጠቃላይ የፖለቲካ አለመረጋጋትና የጸጥታ ችግር አንስተው ይወያዩበታል ብለው እንደሚጠብቁ የፖለቲካ ተንታኙ ይናገራሉ።

"ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን፣በጸጥታውም አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለመገምገም እና የትግራዩን ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያውያን በንፁሃን ዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለው የጅምላ ጥቃትና ጭፍጨፋ ዘርን መሰረት ያደረገ ጨፍጨፋ፣ ለማስቆም መንግስት ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ይመስለኛል።"
,
በዚህ የአንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት አጋጣሚ፣በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በኩል ኢትዮጵያ ከታገደችበትና ሃገራት ከቀረጥና ታሪፍ ነጻ በሆነ መንገድ ምርቶቻቸውን ወደ አሜሪካ ወደ ሚያስገቡበት የአጎዋ ዕድል እንድትመለስ እንዲሁም ተጨማሪ ዕርዳታና ድጎማዎች የሚገኝበትን ጉዳይ እንደሚያነሱ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያና አሜሪካ የ120 ዓመታት የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ በየዘመኑ በተፈጠሩ ክስተቶች ግንኙነቱ አንዴ ሲጠብቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲቀዛቀዝ ታይቷል። በቅርብ ጊዜ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት መነሻነት፣ይኸው ግንኙነት ሻክሮ ቆይቷል።

ግንኙነቱን ወደነበረበት ለመመለስ ገና ብዙ እንደሚቀር እና ለዚህም አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የማደስ ፍላጎት እንዳላት በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ሞሊ ፊ ባለፈው ሳምንት መግለጻቸው ይታወቃል።
ታሪኩ ኃይሉ 
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ