1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ ጌታቸዉ ሹመት፣የሕወሓት ካሸባሪነት መሰረዝ

ሐሙስ፣ መጋቢት 14 2015

"የዚህ ጦርነት ተሳታፊዎች ብዙ ናቸው። ዓላማቸውም እንደዚሁ በጣም የተለያየ ነው። ትግራይ ላይ ወይም ሕወሓት ላይ ተመሳሳይ አቋም የነበራቸው አካላት አብረው ተሰልፈዋል እና ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እነዚህን አካላት አሁንም አንድ ላይ አስተባብሮ ወደ ሰላም ስምምነቱ ማስገባት እና ተገዢ ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ይገባኛል"

https://p.dw.com/p/4P8dO
Äthiopien Friedensabkommen Tigray
ምስል PHILL MAGAKOE/AFP/Getty Images

የሰላም ስምምነቱን ገቢር ማድረጉ እየተቀላጠፈ ነዉ

     

የኢትዮጵያ መንግስትና ሕወሓት ባለፈዉ ጥቅምት 23 ባደረጉት ስምምነት መሠረት ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መሪነት የተሰየሙትን የአቶ ጌታቸዉ ረዳን ሹመት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ አፅድቀዋል።በጦርነቱ ወቅት የወሓት የፖሊት ቢሮና የትግራይ ማዕከላዊ ዕዝ ቃል አቀባይ የነበሩት የአቶ ጌታቸዉ ሹመት የፀደቀዉ ሕወሓት ከአሸባሪ ቡድንነት መዝገብ ትናንት ከተፋቀ በኋላ መሆኑ ነዉ።የአቶ ጌታቸዉን ሹመትና የሕወሃት ከአሸባሪነት መዝገብ መፋቅ መንግስትና ሕወሓት የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ገቢራዊ የማድረጉ ሒደት እየተቀላጠፈ መሆኑን ጠቋሚ ነዉ።

ሁለቱም ባለሙያዎች በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተመስርቶ ስምምነቱ በትክክል እንዲተገበር እነዚህ ውሳኔዎች ከመዘግየታቸው በቀር ተገቢ መሆናቸውን ገልፀዋል።ይሁንና በሕወሓት በኩል ትጥቅ ከመፍታት ጋር ተያይዞ የተነሱበት ተቃውሞዎች፣ የድርጅቱ ከሽብርተኝነት መዝገብ መፋቅ ላይ ከገዢው ፓርቲ አባላት ጭምር የተስተዋሉ ልዩነቶች ለፌዴራል መንግሥቱ የቀጣይ የስምምነቱ አተገባበር ሂደት ፈታኝ ጉዳዮች እንደሚሆኑ ገልፀዋል።የሕወሓት ከአሸባሪ ድርጅትነት መዝገብ መፋቁን እና በክልሉ ይቋቋማል ለተባለው ጊዜያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ መሾማቸው ስለ የተኩስ ማቆም ስምምነቱ የሚኖራቸእን እንደምታን በተመለከተ በቅድሚያ ምልከታቸእው ያጋሩን በመቀሌ ዩኑቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ የትምህርት ክፍል ባልደረባ የሆኑት አቶ ገብረ መድህን ገብረ ሚካኤል ናቸው።
"በትግራይ ክልል ለሚመሠረተው ጊዜያዊ አስተዳደር ለመመሥረት የሕወሓት ፍረጃ መነሳት ግድ ከሆነ ወዲያው መወሰን ከነበረባቸው እርምጃዎች አንዱ ነው። ምክንያቱም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካልተመሠረተ ከብዙ ነገሮች ጋር ተያይዟል። ከበጀት ጋር ተያይዟል፣ ከመንግሥት ሠራተኛ ደሞዝ ጋር ተያይዟል፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቤታቸው ከመመለስ እና ያለመመለስ ጉዳይ ጋርም ተያይዟል፣ እንደዚሁም የትግራይ ግዛትልዊ አንድነትን ከመመለስ እና ከመከላከያ ውጪ በትግራይ አስተዳደር ውስጥ ያሉ ኃይሎችም መውጣት አለመውጣት ጋር ተያይዟል እና ከብዙ ነገሮች ጋር የተያያዘ ስለሆነ ብዙ ነገሮችን ይዞ ስለነበር ቡዘገይም ተወስኗል ወደፊት ሊያስኬድ ይችላል"
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን ሌላኛው የዓለም አቀፍ ሕግ እና የፖለቲካ ተንታኝ ደግም "ትግራይ ውስጥ ያለው ማሕበራዊ ፣ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚጠፋን አይመስለኝም" ካሉ በኋላ ይህንን ችግር ለመፍታት ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት መመስረቱ የግድ ነውና ውሳኔዎቹ ተቀባይነት ያላቸው ናቸው ብለዋል።
"እንዲያውም ዘግይቷል ነው ሊባል የሚችለው። ምክንያቱም ትግራይ ውስጥ ያለፍን ማሕበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚጠፋን አይመስለኝም። ስለዚህ እሱን በተቻለ መጠን ምላሽ ለመስጠት እንዲሞከር ይሄ የሽግግር መንግሥት የሚባለው መቋቋም አለበት። ስለዚህ ዘገየ ካልተባለ ለእኔ ተገቢ ነው ብየ ነው የማስበው። ነገር ግን መነሻው የሕወሓት ከዝርዝር [ አሸባሪነት] መነሳትም ሆነ የትግራይ የሽግግር መንግሥት መቋቋም የሚባለው የፕሪቶሪያ ስምምነት የወለዳቸው ጉዳዮች ስለሆኑ በሌሌቹ የፕሪቶሪያ ስምምነት ጉዳዮች ላይ ያለው እርምጃ ምን ያህል ተሂዶበታል ተብሎ ቢጠየቅ እዚህ ግባ የሚባል ተጨባጭ መረጃ ያለ አይመስለኝም" ብለዋል።
አቶ ገብረ መድህን ገብረ ሚካኤል በፓርቲ ሥራ ውስጥ አብሮ የነበረ አንድ ሰው ስለተቀየረ ብቻ ብዙ መሠረታዊ ለውጦች ይመጣል ብለው እንደማያምኑ ሆኖም ለውጥ አያመጡም ማለት ግን ደግሞ እንደማይቻል የአቶ ጌታቸው ወደፊት የመምጣት ጉዳይ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
የፌዴራል መንግሥቱ አብረውት ከጎኑ ሆነው በጦርነቱ ወቅት ከተሳተፉ አካላት ፈተና ሊገጥመው እንደሚችልም ገልፀዋል።"የዚህ ጦርነት ተሳታፊዎች ብዙ ናቸው። ዓላማቸውም እንደዚሁ በጣም የተለያየ ነው። ትግራይ ላይ ወይም ሕወሓት ላይ ተመሳሳይ አቋም የነበራቸው አካላት አብረው ተሰልፈዋል እና ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እነዚህን አካላት አሁንም አንድ ላይ አስተባብሮ ወደ ሰላም ስምምነቱ ማስገባት እና ተገዢ ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ይገባኛል"አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ የሚቋቋመው ግዚያዊ አስተዳደር እንዲመሩ በህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ተመረጡ።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ሰው ደግሞ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አመሰራረት ጋር በተገናኘ ከትግራይ ክልል ፓርቲዎች ቅሬታ መኖሩ፣ የስምምነቱ ዋና ተዋናይ የአፍሪካ ሕብረት ዝምታ እንዲሁም ከእንደራሴው ምክር ቤት የገዢው ፓርቲ አባላት ልዩነቶች መስተጋባታቸው የቀጣይ ሥራዎችን የሚያከብዱ መሆኑን ገልፀዋል።
ለሁለት ዓመታት ደም ያፋሰሰው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በዝግ ለአሥር ቀናት ንግግር እና ድርድር ከተደረገበት በኋላ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ. ም በተኩስ ማቆም ስምምነት ፊርማ መቋጨቱ ይታወሳል። ያስከተለው ዘርፈ ብዙ ውድመትና ድቀት ግን ቸል የተባለ ይመስላል።

Äthiopien, Addis Abeba | Äthiopisches Parlament
ምስል Solomon Muchie/DW

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ