1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ አበረ ሥርዓተ-ቀብር

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 28 2013

አቶ አበረ ቀድም ሲል በምክትል መቶ አለቃ ማዕረግ የኢትዮጵያ ፖሊስ ባልደረባ ሆነዉ አገልግለዋል። ኤርትራ ሸምቆ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና ኋላ የግንቦት ሰባት አባልም ነበሩም።

https://p.dw.com/p/3t4CM
Äthiopien Beerdigung Abere Adamu
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የአበረ አዳሙ ሥርዓተ-ቀብር

የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የአቶ አበረ አዳሙ የቀብር ስርዓት ዛሬ በባሕርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴደራል ተፈፀመ። አቶ አበረ የክልሉን ፖሊስ በበላይነት በመሩበት ወቅት የኮሚሽኑን አደረጃጀት  በማስተካከል አባላቱን ተጠቃሚ አድርገዋል ተብሏል፡፡አቶ አበረ ቀድም ሲል በምክትል መቶ አለቃ ማዕረግ የኢትዮጵያ ፖሊስ ባልደረባ ሆነዉ አገልግለዋል። ኤርትራ ሸምቆ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና ኋላ የግንቦት ሰባት አባልም ነበሩም።አቶ አረባረ ባሕርዳር ሆስፒታል ዉስጥ ሕክምና እየተደረገላቸዉ ያረፉት ባለፈዉ ማክሰኞ ነዉ።

ዓለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ