1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፤ የአቶ ለማ ልዩነት እና ብልጽግና ፓርቲ

እሑድ፣ ኅዳር 28 2012

ሰሞኑን ይፋ የሆነው የአቶ ለማ ከኢህአዴግ ውህደት እና ከመደመር ፍልስፍና የመለየታቸው ዜና ማነጋገሩ ማስገረሙ ቀጥሏል። ክስተቱ ለህዝብ ጥያቄ ቆመናል የሚሉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አንድ ሆንን ብለው ሳያበቁ፣ የመለያያታቸው ዜና የመከተሉ ልምድ ሌላው ማሳያ ተደርጎ ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል።

https://p.dw.com/p/3UMYf
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Rückblick auf die einjährige Millennium Hall
ምስል Ethiopian Broadcasting Corporation

እንወያይ፦ አነጋጋሪው የአቶ ለማ ልዩነት

ሦስት የኢህአዴግ አባላት  እና 5 አጋር ፓርቲዎች ተዋህደው የብልጽግና ፓርቲ ለመመስረት ስምምነታቸውን በፊርማቸው ካፀደቁ አንድ ሳምንት አልፏል።ይሁንና ሰሞኑን እንደተሰማው ውህደቱ ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር እና ከመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ በኩል ጠንካራ ተቃውሞ ቀርቦበታል።ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ በተጫወቱት ሚና ትልቁን ቦታ የሚይዙት  አቶ ለማ ለአሜሪካ ድምጽ ራድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ  ውህደቱ ትክክል አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።ከውህደት በፊት የአገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮችን መፍታት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ያሉት አቶ ለማ የቅርብ ጓዳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን የመደመር ፍልስፍናንም እንዳልተቀበሉት ነው በዚሁ ቃለ ምልልስ የተናገሩት።ሰሞኑን ይፋ የሆነው የአቶ ለማ ከኢህአዴግ ውህደት እና ከመደመር ፍልስፍና መለየታቸው ዜና ማነጋገሩ ማስገረሙ ቀጥሏል።ክስተቱ ለህዝብ ጥያቄ ቆመናል የሚሉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አንድ ሆንን ብለው ሳያበቁ፣የመለያያታቸው ዜና የመከተሉ ልምድ ሌላው ማሳያ ተደርጎ ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል።የአቶ ለማ ልዩነት እና በብልጽግና ፓርቲ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተጽእኖ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የመለያየት አባዜ የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው።በውይይቱ ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል።እነርሱም ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ጀርመን የሚኖሩ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እና የሕግ ባለሞያ፣ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እንዲሁም አቶ ገረሱ ቱፋ የፖለቲካ ተንታኝ ናቸው። ሙሉውን ውይይት ለመከታተል ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ፦

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ