1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአበበች ጎበና ስርዓተ ቀብር

ማክሰኞ፣ ሰኔ 29 2013

የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ስርዓተ ቀብር በዛሬው እለት ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተፈጸመ፡፡

https://p.dw.com/p/3w7R9
Äthiopien | Beisetzung Abebech Gobena
ምስል Seyoum Getu/DW

በ85 ዓመታቸው ነበር


የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ስርዓተ ቀብር በዛሬው እለት ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተፈጸመ፡፡
በርካታ አሳዳጊ ያጡ ህፃናት እናት የነበሩት የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በኮቪድ-19 ተዋሲ ተይዘው ለአንድ ወር ያህል ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ ከትናንት በስቲያ ማለዳ ህይወታቸው አልፎ ዛሬ በብሔራዊ ክብር ስርዓተ ቀብራቸው ተከናውኗል፡፡
ለአስከሬናቸውም በመስቀል አደባባይ በተደረገው የክብር ሽኝት ስነስርዓት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህምድ የአበባ ጉንጉን በተወካዮቻቸው አስቀምጠዋል፡፡
ከመስቀል አደባባይ እስከ መንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን በተደረገው የክብር ሽኝትም ቁጥራቸው የላቀ የማደጎ ልጆቻቸው እና ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል፡፡ 
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት በተገኙበት በታላቅ ሃይማኖታዊ ፀሎት ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡  
አበበች ጎበኛ በሁለት ህጻናት የጀመሩት የህጻናት ማሳደጊያ ዛሬ ላይ አበበች ጎበና ህጻናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር በሚል ተቋም ቀጥሎ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ዜጎችን የድጋፉ ተጠቃሚ እንዳረጋቸው ይነገራል፡፡

Äthiopien | Beisetzung Abebech Gobena
ምስል Seyoum Getu/DW
Äthiopien | Beisetzung Abebech Gobena
ምስል Seyoum Getu/DW

 

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ 

እሸቴ በቀለ