1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሸባብ የጥቃት ስልት

ማክሰኞ፣ ጥር 14 2011

የሱማሊያው ጽንፈኛ አሸባሪ ቡድን አልሸባብ ባንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በኬንያ እና ሱማሊያ የፈጸማቸው ጥቃቶች ቡድኑ አሁንም ጠንካራ መሆኑን የሚያሳዩ እንደሆኑ በርካታ ተንታኞች እየገለጹ ነው፡፡ ከሳምንት በፊት  መዲና ናይሮቢ በደረሰዉ ጥቃት 20 ሰላማዊ ሰዎች እና አንድ የፖሊስ መኮንን ህይወታቸውን አጥተዋል።

https://p.dw.com/p/3BycI
Kenia Angriff auf Hotel in Nairobi
ምስል Reuters/N. Mwangi

ጥቃት አድራሾቹ ሱማሊያዊ ትውልድ ያላቸው ኬንያዊያን ናቸዉ ተብሎአል

የሱማሊያው ጽንፈኛ አሸባሪ ቡድን አልሸባብ ባንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በኬንያ እና ሱማሊያ የፈጸማቸው ጥቃቶች ቡድኑ አሁንም ጠንካራ መሆኑን የሚያሳዩ እንደሆኑ በርካታ ተንታኞች እየገለጹ ነው፡፡ ከሳምንት በፊት  መዲና ናይሮቢ በደረሰዉ ጥቃት 20 ሰላማዊ ሰዎች እና አንድ የፖሊስ መኮንን ህይወታቸውን አጥተዋል። ከጥቃት አድራሾቹ ውስጥ ደግሞ አምስቱ መገደላቸዉ ይታወቃል። በትናንትናው ዕለትም ኬንያን ከሱማሊያ በሚያዋስናት ድንበር አቅራቢያ፣ ጋሪሳ በተባለ ግዛት የአልሸባብ አባላት እንደሆኑ የተጠረጠሩ ታጣቂዎች ባንድ የቻይና መንገድ ግንባታ ኩባንያ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሞክረው አንድ ሰው ካቆሰሉ በኋላ ጸጥታ ሃይሎች ጥቃቱን መመከታቸው ነዉ የተነገረዉ።
ቻላቸዉ ታደሰ

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ