1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሶሳ፣ የጊምቢ እና ነቀምቴ ነዋሪዎች አዲስ ከሚመሰረተው መንግሥት ምን ይጠብቃሉ?

ቅዳሜ፣ መስከረም 22 2014

የአሶሳ፣ የጊምቢ እና የነቀምቴ ነዋሪዎች አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ለሕዝብ ሰላምና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት በትኩረት ሊሰራ ይገባል የሚል አቋም አላቸው። የጸጥታ ችግሮችን መፍታት፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስና የተዘጉ መንገዶችን ማስከፈት የመሳሰሉ እርምጃዎችም ይጠብቃሉ። ከአዲሱ መንግሥት "ምንም የምንጠብቀው ነገር የለም" የሚሉም አሉ።

https://p.dw.com/p/41AuK
Assosa Town Äthiopien
ምስል DW/N. Dessalegn

የአሶሳ፣ የጊምቢ እና ነቀምቴ ነዋሪዎች አዲስ ከሚመሰረተው መንግሥት ምን ይጠብቃሉ?

በመጪው ሰኞ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት ሊመሰረት ቀነ-ቀጠሮ ተቆርጧል። የአሶሳ፣ የጊምቢ እና የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ለሕዝብ ሰላም እና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት በትኩረት ሊሰራ ይገባል የሚል አቋም አላቸው። ለህብረተሰቡ ስጋት የሆኑት የጸጥታ ችግሮችን መፍታት፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ እና የተዘጉ መንገዶችም ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሶስቱ ከተሞች ነዋሪዎች ከአዲሱ መንግሥት ከሚጠብቋቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል። የዛኑ ያክል ከአዲሱ መንግሥት "ምንም የምንጠብቀው ነገር የለም" የሚሉም ይገኙበታል። የአሶሳ፣ የጊምቢ እና ነቀምቴ ነዋሪዎችን ነጋሳ ደሳለኝ አነጋግሯቸዋል። አስተያየቶቹን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

ነጋሳ ደሳለኝ

እሸቴ በቀለ