1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከሕወሃት ነጻ በወጡ ቦታዎች

ሐሙስ፣ ኅዳር 23 2014

ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቁጥጥር ውጪ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ላይ ከምሽቱ 12 ሰአት እስከ ንጋቱ 12 ሰአት ድረስ የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደንግጓል። በተጠቀሰው ሰአት ማንኛውም ሰው አዋጁ በተጣለባቸው ቦታዎች ለመንቀሳቀስ አይፈቀድለትም ተብሏል።

https://p.dw.com/p/43js5
Karte Sodo Ethiopia ENG

ከምሽቱ 12 ሰአት እስከ ንጋቱ 12 ሰአት ድረስ ይቆያል

ከሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቁጥጥር ውጪ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ላይ ከምሽቱ 12 ሰአት እስከ ንጋቱ 12 ሰአት ድረስ የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደንግጓል።  በተጠቀሰው ሰአት ማንኛውም ሰው አዋጁ በተጣለባቸው ቦታዎች ለመንቀሳቀስ አይፈቀድለትም ተብሏል። በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ቆይተው አሁን በፌደራል መንግሥት ሥር የገቡ የምሥራቅ እና ምዕራብ ግንባር አካባቢዎች ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥሏል።በሌላ በኩል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተግባራዊ መሆን ተከትሎ የተለያየ ጥፋት የተገኘባቸው ሰዎች ላይ ሰነድ የማጠናከርና ምርመራ የማድረግ ሥራ መጠናከሩን የፍትሕ ሚኒስቴር ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት ደግሞ በሁለት ሦስት ቀናት ውስጥ አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ድል የምናበስርበት ጊዜ ከፊታችን ነው በማለት ጦርነቱ የሚገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ ተናግረዋል። 

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ