1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርቲስት ዓለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ-ቀብር

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2013

አድናቂዎቹ ኢትዮጵያዊው «ኤልቪስ ፕሪስሌይ» ሲሉ ያቆላምጡታል። በተስረቅራቂ ነጎድጓዳማ ድምፁ በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ የማይረሱ አሻራዎቹን አሳርፏል። አርቲስት ዓለማየሁ እሸቴ። ዛሬ ስርዓተ ቀብሩ አዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

https://p.dw.com/p/402C0
ምስል Seyoum Getu/DW

ታላቅ ብሔራዊ የአስከሬን አሸኛኘት ስርዓት ተፈጽሞለታል

አድናቂዎቹ ኢትዮጵያዊው «ኤልቪስ ፕሪስሌይ» ሲሉ ያቆላምጡታል። በተስረቅራቂ ነጎድጓዳማ ድምፁ በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ የማይረሱ አሻራዎቹን አሳርፏል። አርቲስት ዓለማየሁ እሸቴ። ዛሬ ስርዓተ ቀብሩ አዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ  ካቴድራል ተፈጽሟል። ከመስቀል አደባባይ እስከ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ድረስም ታላቅ ብሔራዊ የአስከሬን አሸኛኘት ስርዓት ተፈጽሞለታል። በበርካታ ተወዳጅና የሱ ብቻ በሆኑ ለዛ ያላቸው ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው የሙዚቃ ሰው ዓለማየሁ እሸቴ በ80 ዓመቱ ሕይወቱ ማለፉ የተነገረው ባለፈው ሐሙስ እኩለ ሌሊት ነበር። ኢትዮጵያዊው አንጋፋ የሙዚቃ ሰው የአስከሬን ሽኝት ዛሬ ባለስልጣናት፣ የሞያ አጋሮቹ እና ቤተሰቦቹ በተገኙበት በመስቀል አደባባይ  ተከናውኗል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስርዓቱን ተከታትለሎት ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል።    
ሥዩም ጌቱ

Äthiopien Beerdigung Sänger Alemayehu Eshete
ምስል Seyoum Getu/DW

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ