ሙዚቃአፍሪቃ
የአርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ በሙት ዓመቱ ሶስተኛ አልበሙ
እሑድ፣ ሰኔ 27 2013ማስታወቂያ
እውቁ የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ድፍን አንድ ዓመት አለፈው። አርቲስቱ እየሰራበት የነበረው ሶስተኛ አልበሙ ተጠናቆ ባለፈው ሰኞ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሙት ዓመቱ አንድ ቀን ቀድሞ ተለቋል፡፡
“ማል መሊሳ” ሲተረጎም መፍትሄው ምንድነው? በሚል የተሰየመው የአርቲስቱ አልበም 300 ሺህ ጊዜ በሲዲ ታትሞ በአገር ውስጥ እየተሸጠ ይገኛል። በኦንላይን የሙዚቃ ሽያጩም አስደናቂ ስፍራን እየያዘ እንደሆነ ይነገራል። የዛሬ የመዝናኛ ፕሮግራማችን ትኩረቱን በአርቲስቱ ስራዎች በተለይም በአዲሱ አልበሙ ላይ እድርጓል፡፡ አዘጋጁ ስዩም ጌቱ ነው፡፡
ስዩም ጌቱ
ልደት አበበ