የአርበኞች ግንቦት ሰባት አቋም
ማክሰኞ፣ ሰኔ 19 2010ማስታወቂያ
የንቅናቄዉ ሊቀመንበር ዶክተር ብርሐኑ ነጋ ዛሬ በተለይ ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት ለዉጡን ለመቀልበስ የሚሸረበዉን ሴራ ለማክሸፍ ድርጅታቸዉ አበክሮ ይታገላል። ዶክተር ብርሐኑ «በቀድሞዉ ሥርዓት የሚያጋብሱት ጥቅም የቀረባቸዉ ያሏቸዉ ኃይላት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡን ለማወክ የሚያደርጉት ሙከራ እና የሚወስዱት እርምጃ እራሳቸዉን የሚያጠፋ ነዉ ብለውታል። አርበኞች ግንቦት ሰባት ለዉጡን ከአደጋ ለማዳን አስፈላጊዉን ሁሉ እንደሚያደርግም ዶክተር ብርሐኑ አስታዉቀዋል። ዛሬ ብራስልስ ቤልጂግ የሚገኙትን ዶክተር ብርሐኑን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሮአቸዋል። የመጀመሪያዉ ጥያቄ የብራስልስ ጉብኝታቸዉን አላማ የሚመለከት ነበር።
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ