የአፍሪካ የዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ የበርካታ ሴቶችን ህይወት እየቀየረ ነው
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 20 2014ማስታወቂያ
የአፍሪካ የዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ (African Growth and Opportunity Act) የበርካታ ሴቶችን ህይወት በመቀየር ውጤት እያስገኘ ነው ሲሉ በኢትዮጲያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ አወደሱ ።
አምባሳደሯ የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንና ከፓርኩ ሰራተኞች ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል።
የኢትዮጲያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስራ ሃላፊዎቸ በበኩላቸው በውጭ አገራት የሚኖሩ አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች ኢትዮጲያ የአፍሪካ የዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ እያገኘች ያለው ጥቅም እንዲቋረጥ የሚያደርጉት ውትወታ ተገቢነት የሌለው ድርጊት ነው ብለዋል ።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ