የአሜሪካን የሽብር ጥቃት ማስጠንቀቂያና ኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ኅዳር 15 2014ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል የሰጠውን ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አጣጣሉ።ዶቼቬለ ስለ ማስጠንቀቂያው ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ባለስልጣን የከተማዋ ደኅንነት አስተማማኝ ነው ብለዋል።የመንግሥት ኮምኒኬሽን አገልግሎት በበኩሉ የኢትዮጵያውያን ደኅንነት በኤምባሲዎች መግለጫ አይረጋገጥም ሲል መግለጫውን ውድቅ አድርጓል,። የሽብርተኞቹን ማንነት ከማብራራት የተቆጠበው የአሜሪካ መንግስት መግለጫው የሽብር ጥቃቱ ምናልባትም በጥቂት ማሳሰቢያ አሊያም በድንገት የዲፕሎማቶች ማዕከላት፣ የቱሪዚም እና ማጓጓዣ ስፍራዎች፣ በገበያ ማዕከላት፣ የምዕራባውያን የንግድ ተቋማት፣ መዝናኛ እና የመንግስት መገልገየዎችን ትኩረት ሊያድርግ ይችላል ብሏል።
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ