የአሜሪካን ወታደሮች ከጀርመን መልቀቅ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 28 2012ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ ጀርመን ዉስጥ በሚገኙ የጦር ሠፈሮችዋ ካሰፈረቻቸዉ ወታደሮች 12 ሺሕ ያሕሉን ወደ ሌሎች የአዉሮጳ ሐገራት ለማዛወር ወስናለች። የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ጊዜ ጀምሮ የሰፈሩ ወታደሮችን ከጀርመን ለመንቀል የወሰኑት ጀርመን ለሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በቂ ገንዘብ አታዋጣም በሚል ነዉ። ይሁንና ከጀርመን የሚቀነሱት ወታደሮች የሚሰፍሩባቸዉ የአዉሮጳ ሐገራት የጀርመን ለነቶ የሚያዋጡት የገንዘብ መጠን ከጀርመን ያነሰ መሆኑ የትራምን ምክንያት መሠረት አሳጥቶታል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ