የአሜሪካ ጫና በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2014ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ተባብሶ ለቀጠለው ግጭት መልስ ለመስጠት የምጣኔ ሐብት ማዕቀብን ጨምሮ አማራጮችን በማጤን ላይ መሆኗን ዐስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች እንደገለፁት አሜሪካ ለሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተለያዩ አማራጮችን በማየት ላይ ነች። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከአፍሪቃ ኅብረትና አውሮጳ ባለሥልጣናት ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ ውይይት ማድረጋቸውም ተመልክቷል። ሃገራቱ በኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት በአፋጣን የተኩስ አቁም አድርገው ወደ ውይይት እንዲገቡ ሲሉም አሳስበዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ