1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ምርጫ ውጤትና የጀርመን ምላሽ

ሰኞ፣ ጥቅምት 30 2013

መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል አሜሪካና ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ፣ የከባቢ አየር ሙቀት መጨመር እና ሽብርተኝነትን በመከላከል ረገድ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል። የምርጫ ውጤት ከታወቀ በኋላ ጆ ባይደን በአሜሪካ የውስጥና የውጭ ፖሊሲ ለአመታት የዘለቀ ልምድ እንዳላቸው የጠቀሱት ሜርክል ተመራጩ ጀርመንና አውሮፓን በቅጡ ያውቃሉ ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3l3qK
Nach der Präsidentenwahl in den USA
ምስል Michael Kappeler/picture alliance/dpa

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት እና የጀርመን ምላሽ

የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ አሜሪካ እና ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ፣ የከባቢ አየር ሙቀት መጨመር እና ሽብርተኝነትን በመከላከል ረገድ በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል። የአሜሪካ ምርጫ ውጤት ከታወቀ በኋላ ጆ ባይደን በአሜሪካ የውስጥ እና የውጭ ፖሊሲ ለረዥም አመታት የዘለቀ ልምድ እንዳላቸው የጠቀሱት ሜርክል ተመራጩ ጀርመን እና አውሮፓን በቅጡ ያውቃሉ ብለዋል።

መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካሚላ ሐሪስን እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ባለፈው ቅዳሜ ነበር። መርሒተ መንግሥቷ አሜሪካ እና ጀርመን የዘመኑን ፈተናዎች ለመጋፈጥ በጋራ መቆም አለባቸው ብለዋል። ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በአሜሪካ የምርጫ ውጤት ላይ የጀርመን ፖለቲከኞች ስለሰጡት አስተያየት ይልማ ኃይለሚካኤልን አነጋግሬው ነበር።

ይልማ ኃይለሚካኤል
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ