የአማርኛ ፊደላት አጠቃቀም
ሐሙስ፣ ጥቅምት 11 2014ማስታወቂያ
በቅርቡ አትላንታ-ጆርጂያ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ለንባብ የበቃ አንድ የአማርኛ የቋንቋ ሥርዓት መፅሐፍ በጊዜ ሒደት እየደበዘዘ የመጣዉን የቋንቋዉን አጠቃቀም ለማቃናት ጠቃሚ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ። ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ያሳተሙት ይሕ መፅሐፍ የአማርኛ ሞክሼ ሆሕያትንና ዋሕደ ድምፅ ፊደላትን አጠቃቀምና አገባብ በቅጡ ይተነትናል። መፅሐፉ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የሚደረገዉን የፊደላት አጠቃቀም ክርክርን ባይቋጭ እንኳን አንደኛዉ ወገን ሚዛን መድፋቱን የሚያንፀባርቅም ነዉ።
ታሪኩ ኃይሉ
ነጋሽ መሐመድ