1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ፖሊስ በትግራይ ክልል የሚገኝ ኃይል የለኝም አለ

ዓርብ፣ የካቲት 26 2013

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰሞኑን  የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ይውጡ የሚለው መግለጫ የአማራ ክልል ባለስልጣናትን አስቆጥቷል።  መግለጫውን ተከትሎ በትግራይ ክልል  የአማራ ክልል ኃይል እንደሌለ እየገለጹ ነው ።

https://p.dw.com/p/3qGWI
Äthiopien Bahir Dar | Abere Adamu
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የአማራ ክልል ፖሊስ በትግራይ ጉዳይ ላይ የሰጠው ምላሽ

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰሞኑን  የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ይውጡ የሚለው መግለጫ የአማራ ክልል ባለስልጣናትን አስቆጥቷል።  መግለጫውን ተከትሎ በትግራይ ክልል  የአማራ ክልል ኃይል እንደሌለ እየገለጹ ነው ።  ቀደም ሲል ከሕግ አግባብ ውጪ በሌላ አካል ሲተዳደሩ የነበሩ የአማራ አካባቢዎችን መቆጣጠር መቻላቸውንና ያንን አካባቢ ልቀቁ የሚል ክስ ግን ተቀባይነት እንደሌለው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በተለይ ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል። 
ዓለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ