1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ተማሪዎች ችግር

ዓርብ፣ ጥቅምት 5 2014

የአማራ ትምሕርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና የፅሕፈት ቤት ኃላፊ ጌታቸዉ ቢያዝን ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት «ወራሪ» ያሉት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በክልሉ ከ1500 በላይ ትምሕርት ቤቶችን አዉድሟል ወይም ዘርፏል

https://p.dw.com/p/41kAG
Äthiopien Amhara-Region Bildungszentrum
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

አማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት 1ሚሊዮን በላይ ተማሪ አይማርም

                     
በአማራ ክልል ጦርነት በተደረገና በሚደረግባቸዉ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸዉን የክልሉ ትምሕርት ቢሮ አስታወቀ።የአማራ ትምሕርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና የፅሕፈት ቤት ኃላፊ ጌታቸዉ ቢያዝን ለዶቸ ቬለ እንደነገሩት «ወራሪ» ያሉት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በክልሉ ከ1500 በላይ ትምሕርት ቤቶችን አዉድሟል ወይም ዘርፏል።ጦርነት በማይደረግበት አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ ትምሕርት ቤቶችም ከየጦርነቱ ቀጠና የተፈናቀሉ ሰዎች ስለተጠለሉባቸዉ ቢሮዉ የትምሕርቱን ሒደት ለመቀጠል ትልቅ ፈተና እንደገጠመዉ ኃላፊዉ አክለዉ ገልፀዋል።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ