1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወልቃይት ጠገዴና የሰቲት ሁመራ ጉዳይ

ሰኞ፣ ሐምሌ 5 2013

ህወሓት የአማራ ኃይሎች ከምዕራብ ትግራይ ይውጡ እያለ ነው።አቶ ግዛቸው«አካባቢው በትግራይ የተዳደረበት ጊዜ ቢኖር በጉልበት ባለፉት 30 ዓመታት ነው፤ አሁን ጥያቄውን ማንሳት ተቀባይነት የለውም»ብለዋል።ወልቃይት ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ አንድ የአማራ ክልል ዞን ሆኖ አስተዳዳሪዎች በአማራ ክልል ተሸመውለት እየተዳደረ መሆኑን ብቻ እንደሚያውቁ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3wNjr
Äthiopien Gizachew Muluneh General Director Amhara Communication Office Bahar Dar
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የወልቃይት ጠገዴና የሰቲት ሁመራ ጉዳይ

የአማራ ክልል መንግስት የእርዳታ እህል ወደ ትግራይ እንዳይሄድ እየከለከለ ነው የሚለውን ስሞታ እንደማይቀበል የክልሉ መንግስት አስታወቀ።እንደማንኛውም ተሸከርካሪ የእርዳታ እህል የጫኑ ተሸከርካሪዎች ግን እየተፈተሹ ያልፋሉ ብሏል።« የወልቃይት ጠገዴና የአማራ ማንነት ሲጠየቅባቸው የነበሩ ቦታዎችም በአማራ ክልል ስር መተዳደራቸው ይቀጥላልም»ሲል የአማራ ክልል አስታውቋል። ሰሞኑን በአንዳንድ የማህበራዊ ድረ ገፅ ፀሐፍት የአማራ ክልል መንግስት ለትግራይ የሚላክን የእርዳታ አህል የጫኑ ተሸከርካሪዎችን ወደ ትግራይ እንዳያልፉ በተለያዩ አካባቢዎች ክልከላ እያደረገ ነው ሲሉ ተስተውለዋል።ጉዳዩን በማስመልከት ዶይቼ ቬለ የአማራ ክልል የመንግስት ጉዳዮች ኮሙዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህን ጠይቋል።ዳይሬክተሩ “እየተነገረ ያለው ነገር ሀሰትነው” ብለዋል ተሸከርካሪዎቹ ግን በጥብቅ እየተፈተሹ እንደሚያልፉ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል።ክሱ የተለመደ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ግዛቸው፣ ይልቁንም እርዳታው በአስቸኳይ ወደ አካባቢው እንዲደርስ እንተባበራለን ያሉት፡፡የክስ መነሻው ህወሓት ለምን ተሸከርካሪዎች ተፈተሹ ከሚል እንደሆነ የተናገሩት አቶ ግዛቸው፣ አሁን ባለው ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ፍተሻ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አስረድተዋል። «እርዳታ የጫኑ መኪኖች እንዳይፈተሹ የተፈለገው የሚለው» ሌላ ጥርጣሬ የሚያመጣ ነው ያሉት አቶ ግዛቸው ፍተሸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ህወሓት የአማራ ኃይሎች ከምዕራብ ትግራይ ይውጡ እያሉ ነው፣ የክልሉ መንግስት ምላሽ ምን እንደሆነ ዶይቼ ቬለ ዋና ዳሬክተሩን ጠየቆ ነበር፡፡ አቶ ግዛቸው አካባቢው በትግራይ የተዳደረበት ጊዜ ቢኖር በጉልበት ባለፉት 30 ዓመታት ነው፤  ወልቃይት ጠገዴ፣ ሰቲት ሁመራ አንድ የአማራ ክልል ዞን ሆኖ አስተዳዳሪዎች በአማራ ክልል ተሸመውለት እየተዳደረ ያለ አካባቢ መሆኑን ብቻ እንደሚያውቁ ተናግረዋል። 
ዓለምነው መኮንን 
ኂሩት መለሰ
አዜብታደሰ