1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል መንግስት የ «አብን» ሰልፍ ዉድቅ አደረገ

ሰኞ፣ ጥቅምት 16 2013

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በተለያዩ ክልሎች በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን ግድያ ፣ መፈናቀልና መዋከብ በመቃወም የፊታችን ረቡዕ በመላው የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ የአማራ ክልል መንግስት ሕገ ወጥና ሊካሄድ የማይገባው ሲል ከለከለ።

https://p.dw.com/p/3kSvU
Äthiopien | Gizachew Muluneh
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የክልሉ የፀጥታ ኃይል እርምጃ ይወስዳል

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በተለያዩ ክልሎች በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን ግድያ ፣ መፈናቀልና መዋከብ በመቃወም የፊታችን ረቡዕ በመላው የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ የአማራ ክልል መንግስት ሕገ ወጥና ሊካሄድ የማይገባው ሲል ከለከለ። ይህን እያወቁ ወደሰላማዊ ሰልፍ የሚሄዱ ካሉም የክልሉ የፀጥታ ኃይል እርምጃ እንደሚወስድም ገልጿል።የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ዋና ሃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ ማምሻውን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፣«በአሁኑ ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ብለዋል።አቶ ግዛቸው ሰላማዊ ሰልፉ በሁለት ምክንያቶች ሊካሄድ አይገባውምም ብለዋል።


ዓለምነዉ መኮንን 
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ