1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ሁሉም ነገር ለህልውና ዘመቻ » የአማራ ክልል መስተዳድር

ሰኞ፣ ጥቅምት 22 2014

የአማራ ክልል መንግስት ሁሉም የመንግስት ቢሮዎች ተዘግተው ሰራተኛው ወደ ግንባር እንዲዘምት መወሰኑን አስታውቋል፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎችም ወደ አንድ ማዕከል ተሰባስበው ለህልውና ዘመቻው እንዲውል ተወስኗል፣ ውሳኔው የዘገየ ቢሆንም ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ነዋሪዎችና ምሁራን ተናግረዋል፤ ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል፡፡

https://p.dw.com/p/42Qtt
Äthiopien | Yilkal Kefale
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል መንግስት አዲሱ የክተት አዋጅ እና የፖለቲካ ምሁራን እይታ

የአማራ ክልል መንግስት ሁሉም የመንግስት ቢሮዎች ተዘግተው ሰራተኛው ወደ ግንባር እንዲዘምት መወሰኑን አስታውቋል፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎችም ወደ አንድ ማዕከል ተሰባስበው ለህልውና ዘመቻው እንዲውል ተወስኗል፣ ውሳኔው የዘገየ ቢሆንም ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ነዋሪዎችና ምሁራን ተናግረዋል፤ ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል፡፡
የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ትናንት ህወሓት በአማራ ክልል እያደረገ ያለውን ጦርነት ለመቀልበስ የሚያስችል ያለውን የአስቸኳይ ጥሪ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘግተውና በጀታቸውንም ጭምር በማዞር በህልውና ዘመቻው እንዲረባረቡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ሁሉም ተሸከርካሪዎች በአንድ ማዕከል እንዲሰባሰቡና ለጦርነቱ አገልግሎት እንዲውሉ ተወስኗል፡፡
ውሳኔው የዘገየ ቢሆንም ትክክለኛ እርምጃ እንደደሆነ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን መምህሩ አቶ ዘላለም ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ቻላቸው ታረቀኝም ካሁን በፊት የነበሩ የክተት ጥሪዎች ባለቤት ያልነበራቸው እንደነበሩ ተችተው የትናንቱ ውሳኔ በተደራጀና ባለቤት ባለው አመራር የሚመራ መሆኑ ከሌሎች ጊዜ ጥሪዎች የተሸለ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የደብረማርቆሱ ነዋሪ አቶ ጋሻዬ ጌታሁን እንዲሁ የባለፉት የክተት ጥሪዎች ሃላፊነትንና ተጠያቂነትን የማያሳዩ እንደነበሩ አስታውሰው፣ የአሁኑ ውሳኔ የዘገየ ቢሆንም ውሳኔው ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
ችግሩ የሚወገደው በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ብቻ ባለመሆኑ ጦርነቱን በመቀናጀትና በጋራ በመምራት ለድል መብቃት ስፈልጋል ብለዋል አቶ ቻላቸው፡፡
ጦርነቱ በአማራና በአፋር ተወስኖ የሚቀር ባለመሆኑ ሁሉም ክልሎች ተመሳሳይ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አቶ ቻላቸው መክረዋል፡፡
የአማራ፣ የኦሮምያና የደቡብ ክልልሎች ብልፅግና ፓረቲዎች ጦርነቱን ለመቀልበስ ወጣቱ ወደ ግንባር እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ትናንንት የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ባስተላለፈው የአስቸኳ ጊዜ ጥሪ በሁሉም የክልሉ ከተሞች ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ሁሉም እንቅስቃሴዎች ተገድበዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ