1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ እና የሪውቲንግተን ንግድ ማኅበራት ስምምነት

ቅዳሜ፣ ኅዳር 6 2012

የአማራ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራትና በጀርመን አገር የሚገኘው የሪውቲንግተን የኢንድስትሪና ንግድ ዘርፍ ምክርቤት ለሶስት ዓመት የሚቆይ የ 20 ሚሊዮን ብር የንግድ ዘርፍ ትብብር ሰምምነት ተፈራረሙ።

https://p.dw.com/p/3T9ca
Äthiopien Notstände in Amhara
ምስል DW/J. Jeffrey

የአማራ እና የሪውቲንግተን ንግድ ማኅበራት ስምምነት

የአማራ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራትና በጀርመን አገር የሚገኘው የሪውቲንግተን የኢንድስትሪና ንግድ ዘርፍ ምክር ቤት ለሶስት ዓመት የሚቆይ የ 20 ሚሊዮን ብር የንግድ ዘርፍ ትብብር ሰምምነት ተፈራረሙ።

የአማራ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ፕሬዝዳንት መላኩ እዘዘው የስምምነቱን ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል።   በጀርመን አገር የሚገኘው የሪውቲንግተን የኢንድስትሪና ንግድ ዘርፍ ምክርቤት ዳይሬክተር ሚስተር ማርቲን ፋህሊንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በጀርመን መንግስት የልማት ትብብር ትኩረት የተሰጣት አገር መሆኗን አመልክተው ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበር ጋር በእውቀት ሽግግር፣ በልምድ ልውውጥና በልማት ስልቶች በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

«ኢትዮጵያ በጀርመን መንግስት የልማት ትብብር ትኩረት የተሰጣት አገር ናት። ፕሮጀክታችን በጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስትር የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል።  ከአማራ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበር ጋር በመስራታችን በጣም ደስተኞች ነን፣ ወደፊት በአቅም ግንባታ፣ በመዋቅር ማሻሻልና በሌሎችም ዘርፎች በጋራ እንሰራለን። ከዚህ በተጨማሪ በእውቀት ሽግግር፣ በልምድ ልውውጥና በልማት ስልቶች በጋራ የምንሰራ ይሆናል።» ኃላፊው በክልል ደረጃ ከተቋቋመው ከአማራ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበር በተጨማሪ ከሌሎች ዞናዊ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ጋርም በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በንግዱ ዘርፍ እውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በቅርብ ወደ ባህር ዳር እንደሚመጡና ልምዳቸውን እንደሚያካፍሉና ከኢትዮጵያውን ጋር መስራት እንደሚኮራቸውም ሚስተር ማርቲን አመልክተዋል።

የሪውቲንግተን የኢንድስትሪና ንግድ ዘርፍ ምክርቤት ከተመሰረተ 170 ዓመታትን ያስቆጠረ፣ ከ50ሺህ በላይ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ያሉትና ሰፊ ዓለምአቀፍ የትብብር መረብ ያለው ማህበር እንደሆነ በስምምነት የፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጧል።

ዓለምነው መኮንን

እሸቴ በቀለ