የአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ጉብኝት
ሰኞ፣ ሐምሌ 26 2013ማስታወቂያ
የአልጄሪያው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ራምታን ላማምራ ካለፈው ሐሙስ እስከ ቅዳሜ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት እና አስተዳደር ጉዳይ በሚወዛገቡት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ጉብኝት ላይ ቆይተዋል። ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ በአዲስ አበባ ከምክትል ጠቅላይ ምኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን፣ በኻርቱም ከሱዳን አቻቸው መርየም አል-ሳዲቅ እና በካይሮ ከግብጹ ሳሜሕ ሽኩሪ ባደረጓቸው ውይይቶች ኢትዮጵያ እስካሁን አምስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ ያወጣችበት ግድብ ጉዳይ መነሳቱ አልቀረም።
ራምታን ላማምራ በካይሮ ከሳሜሕ ሽኩሪ ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ግንኙነት በወሳኝ ሒደት ውስጥ እያለፈ መሆኑን ተናግረዋል። አልጄሪያ ሶስቱን አገሮች ለማሸማገል ፍላጎት እንዳላት በይፋ የገለጸችው ነገር የለም።
አልጄሪያ ሶስቱን አገሮች የማደራደር ኃላፊነት የተጣለበት የአፍሪካ ኅብረት እና በግድቡ ምክንያት በተቀሰቀሰው ውዝግብ ለግብጽ አደላ እየተባለ የሚወቀሰው የአረብ ሊግ አባል ነች።
ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ