1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኖቤል ሽልማት ለዐቢይ አህመድ

ዓርብ፣ መስከረም 30 2012

የኖርዌይ የኖቤል ተቋም ጠቅላይሚኒስር ዐቢይ አህመድን የዘንድሮው የሰላም ኖቤል ተሸላሚ አድርጓል። ተቋሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ለዚህ ሽልማት ያበቃበት ዋናው ለ20 ዓመታት በድንበር ጉዳይ ሲወዛገቡ የኖሩት ኢትዮጵያ እና የኤርትራ መካከል ሰላም ለማውረድ ባደረጉት ጥረት መሆኑን አመልክቷል።

https://p.dw.com/p/3R9hy
Friedensnobelpreis 2019 an Abiy Ahmed | Bekanntgabe in Oslo durch Berit Reiss-Andersen
ምስል Reuters/NTB Scanpix/Stian Lysberg Solum

አቶ ክቡር ገና

 በሀገር ውስጥ በማካሄድ ላይ የሚገኙ ጠቃሚ ባላቸው ማሻሻያዎችም ጠቅላይ ሚኒስትሩን አወድሷል። ሽልማቱን ይፋ ያደረጉት የኖቤል ተቋሙ ሊቀመንበር በሪት ራይስ አንደርሰን አንዳንዶች ምናልባት ሽልማቱ እጅግ ፈጠነ ሊሉ ቢችሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥረት እውቅና እና ማበረታቻ ይገባል ነው ያሉት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዚህ ሽልማት በመብቃታቸው የግብፅን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት መንግሥታት የእንኳን ደስ ያልዎች መልእክት እየላኩ መሆኑን ዘገባዎች ያሳያሉ። የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ዋና ፀሐፊ የን ሽቶልተንበርግ የጎርጎሪዮሳዊው 2019 ዓ,ም የሰላም ኖቤል ተሸላሚው ዐቢይ አህመድ በትዕግስት፣ በድፍረት እና ሰዎችን በማሳመን ሰላምን ለማምጣት እንደሚቻል ማሳየት» ችለዋል ብለዋቸዋል። የኖርዌይ የስደተኞች ጉዳይ ዋና ፀሐፊ «ዐቢይ አሁን ቀዳሚ ሥራቸው በሀገራቸው ውስጥ በጎሳቸዎች መካከል የሚታየውን ውጥረት መፍታት መሆን እንደሚገባት» አሳስበዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የሰላም ኖቤል መሸለም አስመልክተን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖችን  አነጋግረናል። አቶ ክቡር ገና የኢኒሼቲቭ አፍሪቃ ዳይሬክተር ናቸው። ሌላው ይህንኑ ጉዳይ በማንሳት ያነጋገርኳቸው በኢትዮጵያ ፖለቲካ በንቃት የሚሳተፉት አቶ ግርማ ሰይፉ ይህን ዜና የሰማሁት ብቻዬን አልነበረም ነው ያሉኝ።

Nobelpreisträger Abiy Ahmed

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ