1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እውን ያልሆነው የኔልሰን ማንዴላ ራዕይ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 2010

የደቡብ አፍሪቃ ፀረ ዘር አድልዎ አመራር ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ በዛሬው ዕለት ይሞላቸው ነበር። እኒሁ የነፃነት ታጋይ ከዘር አድልዎ አመራር በተላቀቀችው ሀገራቸው የተለያዩ ዘሮች በአንድነት የሚኖሩበት ህበረተሰብ የመፍጠሩ ራዕይ ነበራቸው ፣ ይሁንና፣ ይኸው ራዕያቸው እሳቸው እንደፈለጉት እውን ሳይሆን ቀርቷል።

https://p.dw.com/p/31dM7
Nelson Mandela 100 Jahre
ምስል picture-alliance/dpa/J. Hrusa

«የአሁኗ ደቡብ አፍሪቃ ሁኔታ ማንዴላን በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ ያሳስባቸው ነበር።»

ደቡብ አፍሪቃ በወቅቱ የምትገኝበት ሁኔታ የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት እና የዘር አድልዎ አመራር ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ እውን ሊያደርጉት ካሰቡት እጅግ የተለየ  እና ቅር ሊያሰኛቸው የሚችል ነው ብለው እንደሚገምቱ  የፕሪቶርያ  ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጥናት ተቋም ዋና ስራ አስኪያጅ ጃኪ ሲልየ ገልጸዋል። 
«  ደቡብ አፍሪቃ  በ2018 ዓም የምትገኝበት ሁኔታ ኔልሰን ማንዴላን አብዝቶ ያሳስባቸው ነበር። »
ብዙ የፖለቲካ ተንታኖችም የሲልየን አስተያየት ይጋራሉ። በዛሬው ዕለት የሚታሰበውን የኔልሰን ማንዴላ 100ኛ ዓመታቸውን ምክንያት በማድረግ በሳቸው ስም የሚጠራው ተቋም እና ገዢው የአፍሪቃውያን ብሔረተኞች ኮንግረስ፣ ኤኤንሲ በመላይቱ ሀገር ለክብራቸው ልዩ መታሰቢያ ዝግጅቶችን እያካሄዱ ነው። ይሁንና፣ ትልቅ ክፍፍል የገጠመው ፓርቲያቸው ቀድሞ የነበረውን ትርጓሜ አጥቷል። የአሁኗ ደቡብ አፍሪቃ  ለውጥ በመሻት ላይ ስትሆን፣ ሀገሪቱ የመጀመሪያው ጥቁር ደቡብ አፍሪቃዊ ፕሬዚደንት ስልጣን ከያዙ ዛሬ ከ24 ዓመታትም በኋላ የተሻለ እድል ፍለጋ ስትጥር ትታያለች።  በዚህም የተነሳ ኔልሰን ማንዴላ በደቡብ አፍሪቃ  የተለያዩ ዘሮች በጋራ የሚኖሩበት ማህበረሰብ ለመፈጠር የወጠኑት እቅዳቸውም፣ በተለይ ስማቸው ከሙስና ቅሌት ጋር በተያያዘ አዘውትሮ የሚነሳው የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ ተጠያቂ እንደሆኑ ነው ጃኪ ሲልየ የሚናገሩት።
«ጄኮብ ዙማ  በፕሬዚደንትነት በቆዩባቸው ዓመታት በሀደሪቱ ላይ ብዙ ጉዳት አድርሰዋል። ሀገሪቱ  በተለይ በብሔራዊው አንድነት ላይ ትልቅ ጉዳት ደርሶባታል። ዛሬ ደቡብ አፍሪቃ ተከፋፍላለች፣እርግጥ፣ የወደፊት ሁኔታዎች  አዎንታዊ ናቸው።  ግን፣ ደቡብ አፍሪቃ ጄኮብ ዙማ በሙስና፣ ዘመድ አዝማድ በመጥቀሙ አሰራራቸው እና በዘገምተኛው የኤኮኖሚ እድገት ካደረሱባት ጉዳት እስክታገግም ድረስ ብዙ ዓመታት ያስፈልጓታል። » 
ካለፈው የካቲት ወር፣ 2018 ዓም ወዲህ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት የማንዴላ ታማኝ የሚባሉት ሲሪል ራማፎዛ  የማንዴላን ከዘረኝነት የጸዳ ማህበረሰብ የመፍጠሩን ራዕይ እውን ማድረግ ሊሳካላቸው እንደሚችል ጃኪ ሲልየ ይገምታሉ። ማንዴላ ለተተኪነት ያሰቧቸው ራማፎዛ የሀገሪቱ ለዘብተኛ እና ዘመናይ ሕገ መንግሥት በተረቀቀበት ስራ ላይ ተሳታፊ ነበሩ።  ሲልየ በዘረኝነት በተከፋፈለው ማህበረሰብ መካከል እርቅ በመፍጠሩ ተግባር ላይ አትኩረዋል ያሏቸው ማንዴላ በሀገሪቱ የተጓደለውን ማህበራዊ እኩልነት፣ አሁንም፣ በጥቂት n።ጮች እጅ የሚገኘውን መሬት ክፍፍልን፣ መሬታቸው የተወሰደባቸው ነጮች ገበሬዎችን ካሳ መስጠትን ለመሳሰሉ ጥያቄዎች መፍትሄ ፍለጋውን ወደጎን መተዋቸው ዛሬም በሀገሪቱ  ትልቅ ችግር እንደደቀኑ ይገኛሉ፣ ለዚህ ግን ማንዴላ ብጸናው ተጠያቂ አይደሉም ባይ ናቸው።  ችግሩ በዘጠኝ ዓመቱ የዙማ አመራር ዘመን ተባብሷል።  ይሁንና፣ ማንዴላ በስልጣን በቆዩባቸው አምስት ዓመታት የታዩትን የአዲሷን ደቡብ አፍሪቃ ችግሮች በሚገባ አልታገሉም በሚል ብዙ ወጣት ደቡብ አፍሪቃውያን ያሰሙትን አስተያየት በማጣጣል፣ በነጮች እና በጥቁሮች መካከል የርስበርስ ጦርነት እንዳይነሳ ማከላከል የተሰኘውን ዋነኛ ዓላማቸውን ገሀድ ማድረጋቸውን አድንቀዋል።  ይህንኑ የጃኪ ሲልየ አስተያየት የሚጋሩት በፕሪቶርያ የሚገኘው የዊትዎተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት አዳም ሀቢብ ማንዴላ የሰሯቸውን  ስህተቶች ለመቀበል እንደማይቸገሩ አስታውቀዋል።
« የአሁኗ ደቡብ አፍሪቃ ሁኔታ ማንዴላን ቢኖሩ ኖሮ እንደሚያሳስባቸው አምናለሁ፣ ይሁን እንጂ፣ በአስተዳደራቸው ዘመን አንዳንድ ስህተቶች  መሰራታቸውን ፣ ለምሳሌ፣ ወግ አጥባቂውን የኤኮኖሚ መርሀግብር መከተላቸውን የማህበራዊ እኩልነት መጓደልን እንዳባባሳው አምነዋል። ይህ ስህተት በህብረተሰቡ ዘንድ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ክፍፍል አስከትሏል። ይህ ግን በሌላው የዓለም አካባቢም የሚታይ ክስተት ነው። »

Südafrika - neuer Präsident Cyril Ramaphosa – Vereidigung
ምስል Reuters/M. Hutchings

 አርያም ተክሌ /ማርቲና ሺቭኮብስኪ

አዜብ ታደሰ