የኒዎ ናዚ አመለካከት ሰለባ የሆኑት የጀርመን ፖሊሶች
ሐሙስ፣ መስከረም 7 2013ማስታወቂያ
በምዕራባዊ የጀርመን ፌዴራላዊ ግዛት ቬዝት ቫሊያን የቀኝ ጽንፈኞችን ፕሮፖጋንዳ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ሲያስተላልፉ ነበር የተባሉ 29 የፖሊስ አባላት ከስራቸው ታገዱ።ፖሊሶቹ ዋትስ አፕ የተባለውን የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ በመጠቀም የኒዎ ናዚ አስተሳሰብን የሚደግፉ የተለያዩ መረጃዎችን ሲያስተላልፉ ነበር ተብሏል። ከሥራቸው የታገዱት ፖሊሶቹ ከሙያ ስነምግባር ባፈነገጠ ክልክል ተግባር ላይ በመሰማራታቸውም ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ይልማ ሃይለሚካኤል
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ