1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን ለመታደግ የጋራ ፕሮጀክት

ሰኞ፣ ጥር 24 2013

ትናንት ይፋ የተደረገውን ፕሮጀክት በፌደራል መንግስት፣ በደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ 48 ባለድርሻ አካላት አጽድቀውታል።በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ገቢራዊ ይሆናል የተባለው ፕሮጀክት አሁን ፓርኩ የተጋረጠበትን ህገ ወጥ ሰፈራ የወሰን መካለልና ከተፈጥሮ ሀብት መመናመን ጋር በተያያዘ ያሉበትን ችግሮች ይቀርፋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ። 

https://p.dw.com/p/3ogTA
Wald in Süd Äthiopien,
ምስል DW/ Shewangizaw W

የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን ለመታደግ ያስችላል የተባለ የጋራ ፕሮጀክት

ህልውናው በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክን ለመታደግ ያስችላል የተባለ የጋራ ፕሮጀክት ስምምነት ይፋ ተደረገ ።ትናንት አርባ ምንጭ ላይ ይፋ የተደረገውን ፕሮጀክት በፌደራል መንግስት፣ በደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ 48 ባለድርሻ አካላት በስምምነት አጽድቀውታል።በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ገቢራዊ ይሆናል የተባለው ፕሮጀክት አሁን ፓርኩ የተጋረጠበትን ህገ ወጥ ሰፈራ  ፣ የወሰን መካለልና ከተፈጥሮ ሀብት መመናመን ጋር በተያያዘ ያሉበትን ችግሮች ይቀርፋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። 


ሸዋንግዛው ወጋየሁ 


ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ