1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነአቶ ጃዋር ቅሬታ እና የኮሮና ስጋት

ዓርብ፣ ሐምሌ 17 2012

እስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ «ኦፌኮ» ባለስልጣናት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የሚገኙባቸዉ አራት ተጠርጣሪዎች እስር ቤት የሚገኙበት ሁኔታ ለጤናቸዉ አስጊ የሆነ ነዉ ሲሉ ጠበቃጠዉ ተናገሩ። አቶ ደጀኔ ጣፋ ኤካ የኮሮና ማገገምያ ናቸዉ ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/3fscV
Deutschland Äthiopiens Oromo federalist congress |  Dejene Taffa
ምስል Eshete Bekele Tekele/DW

የታሰርነዉ ለየብቻችን ነዉ፤ አቶ ደጀኔ ጣፋ ኮሮና ማገገሚያ ገብተዋል

እስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ «ኦፌኮ» ባለስልጣናት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የሚገኙባቸዉ አራት ተጠርጣሪዎች እስር ቤት የሚገኙበት ሁኔታ ለጤናቸዉ አስጊ የሆነ ነዉ ሲሉ ጠበቃጠዉ ተናገሩ። የታሰሩበት ክፍል መብራት የሌለዉ መብራት ሲጠፋም ሻማ እንደማይገባላቸዉ፤ ብሎም እርስ በርስ እንዳይገናኙ ተለያይተዉ መታሰራቸዉን ጠበቃዉ አክለዋል። በሌላ ዜና በቁጥጥር ስር የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ «ኦፌኮ» የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ደጀኔ ጣፋ በኮሮና መያዛቸዉ መመረጋገጡ ወደ ኤካ የኮሮና ማገገሚያ መዛወራቸዉ ተነግሮአል። ከዓለም ዜና እንደተከታተልነዉ የኢዴፓ መስራችና አባል አመራር እና የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ብሎም አብሮነት በሚባለው የፓርቲዎች ጥምረት የኢዴፓ አስተባባሪ ተወካይ አቶ ልደቱ አያሌዉ ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነግሮአል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዘገባዎችን አሰባስቦ ልኮልናል።

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ