የችኩንጉኒያ ወረርሽ በድሬዳዋ
ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2011ማስታወቂያ
ዕዉቁ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ዓሊ ቢራ «ድሬዳዋ እየኖርን ጅቡቲ ምንያደርግልናል» እያለ በያዚያ በራቀዉ ዘመን ከጅቡቲ ጋር ያነፃፀራት ምሥራቃዊቱ ኢትዮጵያዊት ከተማ ድሬዳዋ፣ ዛሬ ትንኝ ማጥፋት አቅቷት ችኩንጉኒያ ለተባለ ወረርሽኚኝ የነዋሪዎችዋን ጤና እየገበረች ነዉ። ከሁለት ሳምንት በፊት ነዋሪዎችን መልከፍ እንደጀመረ የሚታመነዉ ወባ መሠል በሽታ በአጭር ጊዜ፣ በመላዉ ከተማይቱ ተሰራጭቷል። የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ እንደታዘበዉ ችኩንጉኒያ ድሬዳዋ ዉስጥ ያላንኳኳዉ ቤት፣ ያላተኮሰዉ ሰዉ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ። የከተማይቱ ጤና ቢሮ እንደሚለዉ እስከትናንት ድረስ በትንሽ ግምት ከ7ሺሕ በላይ ሰዉ በበሽታዉ ተለክፏል። የሞተ ስለሞኖር አለመኖሩ ግን እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
,መሳይ ተክሉ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ