የቻይናው የማንደሪን ቋንቋ በኢትዮጵያ የትምሕርት ሥርዓት
ቅዳሜ፣ ሰኔ 6 2018
ኢትዮጵያእና ቻይና ማንደሪንን በመባል የሚታወቀውን የቻይና ቋንቋ በአኢትዮጵያ የተምህርት ሥርዓት ውስጥ በማካተት ለማስተማር ተስማምተዋል። ይህ የቻይና ቋንቋ በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ዕድሎች እንዳሉት ሁሉ ስጋቶችም ፈጥሮል። የተቀርፅውን ሥርዓተ ትምህርት በአግባቡ እናስተምር ቢባል መፃሀሕፍትና ቤት እና ቤተ ንባብ ይኖረናል ወይ ብለው የሚጠይቁ አሉ። ሌሎች ደሞ ቋንቋውን መማር ለወጣቱ ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል ይላሉ። ለዶይቸቬለ አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የቋንቋ ሙሁር አዲሱ የትምህርት ሥርዓት የሚፈቅደው ነው ብለዋል።
የትምህርቱ ትሩፋት
ኢትዮጵያ እና ቻይናየቻይናን ቋንቋ የሆነውን ማንዳሪን በኢትዮጵያ ብሔራዊ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ለማካተት የ 5 ዓመት ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህ ውሳኔ በሀገሪቱ የትምህርት ፖሊሲ፣ የውጭግንኙነት እና የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያለው በመሆኑ ሰፊ ክርክር አስነስቷል። የዚህ ስምምነት ደጋፊዎች ውሳኔውን ከወቅቱ ዓለም አቀፋዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተያያዘ መሆኑን ይገልጻሉ። ቻይና በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የኢኮኖሚ አጋር ናት። በመሆኑም ቋንቋውን መማር ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በቻይና ኩባንያዎች፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እናበዲፕሎማሲው ዘርፍ ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል።
በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የትምህርት እና የቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር የቆየአለም ደሴ ለዶይቸቨለ በሰጡት አስተያየት፤ ቻይና በቴክኖሎጂ እና በኢንዱስትሪ ያላትን ዕውቀት በቀጥታ ለመቅሰም፣ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዕድል እና የምርምር አቅምን ለማስፋት ትልቅ ድልድይ ይሆናል ብለዋል። ይህም ተማሪዎችን በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል።
«የውጭ ቋንቋማከል በተማሪዎች ላይ ጫና ይፈጥራል»
በሌላ በኩል ሀገሪቱ አዲሱን ብሔራዊ ሥርዓተ-ትምህርት እየተገበረች ባለችበት እና የሀገር ውስጥቋንቋዎችን በትምህርት ላይ ለማካተት እየሞከረጭ ባለችበት ወቅት፣ ሌላ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋማከል በተማሪዎች ላይ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ነው። ማንዳሪንን ማስተማር የሚችሉ በቂ የሀገርውስጥ መምህራን እና መጻሕፍት በሌሉበት፣ ይህንን ፕሮግራም ለማስፈጸም የሚወጣው ከፍተኛሃብት ለሌሎች መሠረታዊ የትምህርት ጥራት ማሻሻያዎች ቢውል አይሻልም ስል ላቀረብኩላቸው ጥያቂ ዶ/ር የቆየአለም ሲመልሱ
ይህ ስምምነት ለኢትዮጵያ ወጣቶች አዳዲስ የዓለም አቀፍ ዕድሎችን የሚከፍት ቢሆንም፣ የሀገርውስጥ የትምህርት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ሳይጋፋ እና ተጨማሪ ጫና ሳይፈጥር በጥንቃቄ መተግበር እንዳለበት ዶ/ር የቆየአለም ደሴ መክርዋል።
ሐና ደምሴ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር