1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሙዚቃ

የትግርኛ ሙዚቃው ንጉስ ኪሮስ ዓለማየሁ ሲታወስ

እሑድ፣ ጥቅምት 23 2012

አንጉዐይ ፍስስ፣ ምቅናይ፣ ሀቢ ክራር፣ ኣይመነኩዋን የተሰኙት የኪሮስ ዓለማየሁ የሙዚቃ ሥራዎች ዛሬም ከሚደመጡ መካከል ናቸው። ሐምሌ 19 ቀን 1944 ዓ.ም.ተወልዶ በ 1986 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ኪሮስ በማራኪ ለዛና ድምፁ ጥልቅ የሙዚቃ ግጥሞቹ፣በድንቅ የባህል ሙዚቃ መሳሪያዎች ችሎታው ተለይቶ ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/3SOgJ
Symbolbild Mikrophon auf der Bühne
ምስል picture-alliance/Bildagentur-online/Tetra

መዝናኛ፤ ኪሮስ ዓለማየሁ ሲታወስ

በሚደነቅ የሙዚቃ ክህሎት፣ ልዩ የትግርኛ ምት እስክስታ ችሎታ፣ በባህላዊ አለባበሱና ፀጉር አሰራሩ፣ ማራኪ ለዛና ድምፁ ከዛም አልፎ ጥልቅ የግጥም ይዘትና ድንቅ የባህል ሙዚቃ መሳሪያዎች ችሎታው ብዙዎች የሚያውቁት አርቲስት ኪሮስ አለማየሁ ውልደቱና እድገቱ ትግራይ ክልተ አውላዕሎ አውራጃ አካባቢ ነው።

ኪሮስ አለማየሁ ሐምሌ 19 ቀን  1944 ዓ.ም. ከእናቱ ወይዘሮ ቀለብ ገብረመስቀል እና ከአባቱ ግራዝማች አለማየሁ መለስ በትግራይ ክልተ አውላዕሎ አውራጃ ተወለደ። የስለት ልጅ ኪሮስ አንደኛ ደረጃ ትምህርቱ በተከታተለባቸው ስንቃጣና ውቅሮ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በነበረው ቆይታ ከመደበኛ ትምህርት ጉብዝናው በተጨማሪ የሙዚቃ ችሎታው ያሳየባቸው መድረኮችም እንደነበሩ አብሮአደጎቹ ይናገራሉ።

ኪሮስ አለማየሁ በአጭር ግዜ 6 ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞች ለህዝብ በማቅረብ በመላ ኢትዮጵያ አድናቆት ያተረፈ አርቲስት ነው። አንጉዐይ ፍስስ፣ ምቅናይ፣ ሀቢ ክራር፣ ኣይመነኩዋንና ሌሎች ስራዎቹ አሁንም ድረስ ተደማጭና ተወዳጅ ናቸው። ኪሮስ በአድናቂዎቹ ዘንድ የትግርኛ ሙዚቃ ንጉስ ተብሎ ይጠራል።

ከአንድም ሁለቴ በእስር ቤቶች አሰቃቂ የእስር ጊዜ ያሳለፈው አርቲስት ኪሮስ አለማየሁ 1986 ዓ.ም ጥቅምት ወር ነበር በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው። ከአራት ዓመት በፊት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ኪሮስ አለማየሁ የክብር ዶክትሬት ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።

ሙሉ መሰናዶውን ለማድመጥ የሚከተለውን መስፈንጠሪያ ይከተሉ

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

እሸቴ በቀለ