የትግራይ ክልል ውሳኔ
ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2012ማስታወቂያ
የትግራይ ክልል መንግስት አዲስ የአንደኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አማራ ክልል ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንደማይገቡ ገለፀ፡፡ ስለ ጉዳዩ መግለጫ የሰጡት የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ሐላፊ ዶክተር ገብረመስቀል ካሕሳይ የትግራይ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች በአማራ ክልል በሚገኙ 10 ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውውን ተናግረው ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንዲቀየሩ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።ተማሪዎቹ ወደ አማራ ክልል እንዳይሄዱ የሚደረገውም በግጭት ስጋት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል። ከመቀሌ ዝርዝር ዘገባ ተዘጋጅቷል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ