የትግራይ ምክር ቤት ጉባኤ ተጠናቀቀ
ሰኞ፣ ጥቅምት 12 2011ማስታወቂያ
ዛሬ የተጠናቀቀው የሦስት ቀኑ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ፤ አፈ ጉባኤውን አሰናብቶ የካቢኔሹም ሽር አድርጎ ዘጠኝ አዳዲስ ሰዎችን መሾሙም ተገልጿል። በትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አቅራቢነት 9 የቢሮ ኃላፊዎችና 3 የዞን አስተዳዳሪዎች ምክር ቤቱ ሹመታቸው አፅድቋል፡፡ ከዘጠኙ አዳዲስ የካቢኔ አባላት መካከል 6 ሴቶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የቀድሞ የደህንነት ሐላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር የድህንነትና ፀጥታ አማካሪ ሆነዋል፡፡ ለ2011ዓ,ም የሚያከናውነውን እቅድ በማቅረብም አፀድቋል። ከመቀሌ ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ