1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ ርዳታ፣ የኢትዮ-ሱዳን ዉዝግብና ኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ የካቲት 16 2013

የኢትዮጵያ መንግስት፣ ትግራይ ክልል ዉስጥ በተደረገዉ ዉጊያ ለችግር ለተጋለጠዉ ሕዝብ ርዳታ ለማቅረብ ለጠየቁ ለ75 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፈቃድ መስጠቱትን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3plK6
Ethiopia Addis Abeba Botschafter Dina Mufti
ምስል Author Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ መንግስት፣ ትግራይ ክልል ዉስጥ በተደረገዉ ዉጊያ ለችግር ለተጋለጠዉ ሕዝብ ርዳታ ለማቅረብ ለጠየቁ ለ75 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፈቃድ መስጠቱትን አስታወቀ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት 75 ድርጅቶች ፈቃድ ቢያገኙም እስካሁን ለትግራይ ሕዝብ ከሚሰጠዉ ርዳታ 70 በመቶዉን የሚሰጠዉ የኢትዮጵያ መንግስት ነዉ።ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የገጠመችዉን የድንበር ዉዝግብ በድርድር ለመፍታት አሁንም ዝግጁ መሆንዋን ቃል አቀባዩ አስታዉቀዉ ለመደራደር ግን አወዛጋቢዉ ድንበር አካባቢ በፊት የነበረዉ ወደነበረበት መመለስ አለበት-አምባሳደሩ እንዳሉት።   

ሰለሞን ሙጪ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ