1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ መንግሥት ተቃዋሚዎች ሥጋትና ዉግዘት

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 22 2012

የትግራይ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ያስተላለፉትን ማስጠንቀቂያ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ነቀፉት።

https://p.dw.com/p/3VZMO
Äthiopien | TPLF Konferenz in Mekele
ምስል DW/M. Hailesilassie

«የትግራይ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ያስተላለፉትን ማስጠንቀቂያ»

                
የትግራይ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ያስተላለፉትን ማስጠንቀቂያ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ነቀፉት። ዶክተር ደብረፂዮን መቀሌ ዉስጥ የመከረ ጉባኤን ሲከፍቱ «የትግራይን ሠላም የሚያዉኩና የሕዝቡን አንድነት የሚበትኑ፣ ባንዳ» ያሏቸዉን ግን  በስም ያልጠቀሷቸዉን ወገኖች፣ መንግስታቸዉ እንደሚቀጣ ዝተዋል። የተቃዋሚዉ የአረና ትግራይ ፖለቲከኛ ዛቻዉን፣ ሕዝብን የሚያስጨንቅ «ወንጀል» ሲሉት፣ የሳልሳዊ ወያኔ ፓርቲ ባለስልጣን እንዳሉት ደግሞ የምክትል ርዕሠ መስተዳድሩ ንግግር «ጥንቃቄ የጎደለዉ» ነዉ። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባል ንግግሩ፣ በትግራይ ክልል ከሕወሓት ዉጪ ሌሎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚገድብ በማለት ተቃዉመዉታል። የአሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ባወጣዉ መግለጫ ደግሞ ሕዝቡን ላልተገባ ስጋት የሚዳርግ በማለት ነቅፎታል። ለዝርዝሩ የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ ።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ