1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የትምሕርት ፍኖተ ካርታና የትግራይ ተቃዉሞ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 21 2011

በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የቀረበው አማርኛን ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ የማስተማር እቅድ ግን "ፍፁም ተቀባይነት የለዉም" ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ዙርያ ተጨማሪ ሐሳቦችም ተቃውሞ እንዳለው አመልክቷል፡፡

https://p.dw.com/p/3OZ2t
Äthiopien Bildungsbüro der Region Tigray
ምስል DW/Million Haileselassie

የትግራይ ክልል የትምሕርት ፍኖተ ካርታዉን በከፊል ተቃወመ

ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋን ካንደኛ ክፍል ጀምረዉ ይማሩ የሚለዉን የትምሕርት ሚኒስቴርን አዲስ ደንብ የትግራይ መስተዳድር ትምሕርት ቢሮ ዉድቅ አደረገዉ።የኢትዮጵያ የትምሕርት ሚኒስቴር ባለፈዉ ሳምንት ይፋ ባደረገዉ የትምሕርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ አማርኛ ቋንቋ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ ይደነግጋል።የትግራይ ትምሕር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ባሕታ ወልደ ሚካኤል እንደሚሉት ግን የአማርኛና የትግሪኛ ፊደላት አንድ በመሆናቸዉ አማርኛ በክልላቸዉ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጥ የሚለዉ ደንብ «ፍፁም» ተቀባይነት የለዉም።የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናም በብሔራዊ ደረጃ እንዲሰጥ ትምሕርት ሚኒስቴር መደንገጉንም የትግራይ ትምሕርት ቢሮ ዉድቅ አድርጎታል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ እንደገለፀው እስካሁን በክልሉ ከሶስተኛ ክፍል ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ለተማሪዎች ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በቀጣይ ጥናት ተደርጎ ለውጥ ሊደረግበት እንደሚችልም ጠቁሟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ ይፋ በተደረገው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይም ተቃውሞ እንዳለው የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልፀዋል፡፡
በቅርቡ በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ይፋ በተደረገው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ማብራርያ የሰጡን የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሐላፊ አቶ ባህታ ወልደሚካኤል ፍኖተ ካርታው በተለይም የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ ማለቱ በትግራይ ክልል በኩል ተቀባይነት እንደሌለው ገልፀዋል፡፡ ላለፉት ዓመታት በትግራይ ክልል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት እየተሰጠ የቆየው ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ መሆኑ የገለፁት ምክትል ሐላፊው "አንዳንድ ምሁራን ዘንድ ከ5ኛ አልያም 7ተኛ ክፍል ጀምሮ መሰጠት አለበት" የሚል ሐሳብ እየቀረበ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተማሪዎች ከስምንተኛ ክፍል ጀምረው አማርኛ ቋንቋ ይማሩ የሚለው ውሳኔ የሚሰጠው ግን ጥናት ተደርጎ ነው ሲሉ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሐላፊ አቶ ባህታ ወልደሚካኤል ገልፀዋል፡፡

 በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የቀረበው አማርኛን ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ የማስተማር እቅድ ግን "ፍፁም ተቀባይነት የለዉም" ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በአዲሱ ፍኖተ ካርታ ዙርያ ተጨማሪ ሐሳቦችም ተቃውሞ እንዳለው አመልክቷል፡፡ ስምንተኛ ክፍል ለጨረሱ የሚሰጠው ፈተና 'አገር አቀፍ ፈተና' ለማድረግ መታቀዱ፣ በትምህርት ፍኖተ ካርታው ዙርያ የጋራ መግባት ሳይደረስ ወደ ትግበራ ለመሸጋገር የሚደረግ ጥረት ተቀባይነት የለውም ብሏል፡፡ 

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በፍኖተ ካርታው ዙርያ ያለውን ተቃውሞ ለትምህርት ሚኒስቴር ማቅረቡን የገለፀ ሲሆን እስካሁን ግን ምላሽ አልተሰጠኝም ብሏል፡፡ ከነገ በስትያ ሐሙስ ጀምሮ በሚካሄደው ሀገርአቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ ፍኖተ ካርታው አንዱ መወያያ ርእስ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል፡፡

ሚሊዮን ኃይለስላሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋለም ወልደየስ

 


--