የትምሕርት ዘርፉ ሥርዓታዊ መፍትኄ ያሻዋል ተባለ
ሐሙስ፣ መጋቢት 29 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ሥርዓታዊ ችግር ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ሥርዓታዊ መፍትኄ ያስፈልገዋል ሲል የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ተናገረ። የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ የመሥሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ ከአባላቱ ለተነሳላቸው በርከት ያሉ ጥያቄዎች ሲመልሱ የትምህርት ሥርዓቱ መሠረታዊ የግብረገብነት ክስረት ውስጥ ገብቷል ብለዋል። ይህንን ለማስተካክልም ትምህርት እና ፖለቲካ ሊለዩ፣ ዘርፉ ከእየ አካባቢነት ፉክክርም ሊለይ ይገባል ብለዋል። የብዙ ትማሪዎችን ሕይወት መጉዳቱ በስፋት የመወያያ ርእስ የሆነው የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ፈተና ጉዳይም ጥያቄ ተነስቶበት ነበር።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ