1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

የትምህርትን ጥራት ማሳደግ ላይ ያለመ የትብብር መድረክ

ረቡዕ፣ መስከረም 21 2012

የኢትዮጵያ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ የሚገኙ የአምባሳደር ማኅበረሰብ አባላት እና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር በዘርፉ  ትብብር እንዲያሳድጉ  ያለመ ውይይት ትናንት አካሂዷል።

https://p.dw.com/p/3Qext
Äthiopien | Treffen des Ministeriums für Technologie und Wissenschaft zu Fortschritt in Äthiopien
ምስል DW/G. Tedla

የትምህርትን ጥራት ማሳደግ ላይ ያለመ የትብብር መድረክ

 ኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርት አቅርቦት እና ተደራሽነት እየተስፋፋ መሄዱ ቢታመንም ጥራቱን ለማሻሻል ከሌሎች ዓለም አቀፍ አቻ ተቋማት ጋር የትብብር ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተነግሯል። ኢትዮጵያ ታሪካዊ ሀገር እንደመሆኗ ለጥናት እና ምርምር ዘርፉ የምታበረከትው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ እንዲህ ያሉት መድረኮች ዕድሉን ያመቻቻሉ ተብሎ እንደሚታመንም ተገልጿል። ጉባኤውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ለዕለቱ የሳይንስ እና ቴክኒዎሎጂ መሰናዶ ተከታዩን ጥንቅር ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ