1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቴሌኮም ዘርፍ አዲስ መንገድ

ማክሰኞ፣ መስከረም 4 2014

በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ የሆነውን የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻን ወደ ግል ለማዞር የወጣው የመወዳደሪያ ሐሳብ መጠየቂያ ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ተደርጓል።

https://p.dw.com/p/40J6i
Äthiopien Addis Abeba | Ethio Telecom building
ምስል DW/H. Melesse

ፍላጎታቸውን የገለፁም ሆነ ሌሎች እንዲጫረቱ ጥሪ ቀርቧል

በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ የሆነውን የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻን ወደ ግል ለማዞር የወጣው የመወዳደሪያ ሐሳብ መጠየቂያ ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ተደርጓል። የሐሳብ መጠየቂያው ለሁሉም ለሚመለከተው ክፍት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ በፊት የፍላጎት መግለጫ በማቅረብ ፍላጎታቸውን የገለፁም ሆነ ሌሎች እንዲጫረቱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ መንግሥት ይህንን ድርሻ ወደ ግል ከማስተላለፉ በፊት የኩባንያውን ትክክለኛ የሃብት መጠን በጥንቃቄ ማጥናትና ምናልባት ወደፊት ሊቀነሱ ስለሚችሉ ሠራተኞች ጉዳይም ከወዲሁ መፍትሔ ሊያዘጋጅ ይገባል ብለዋል። የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን በበኩሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የተደረገን ዓለም አቀፍ ጨረታ በግልፅነት ማከናወኑን በስኬት ጠቅሶ ወደፊት በዘርፉ ላይ የቁጥጥር ሥራዎችን በሚገባ ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ