1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታከለ ኡማ፤ የህወሃት እንዲሁም የአማራ ክልል የፀጥታ ጉዳይ

ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2012

«ታከለን ስቃወም ነው የቆየሁት አሁን ሊነሳ ነው ሲባል ደብሮኝ ነበር እንኩዋን ተመለስክ በኢትዮጵያዊነትህ ቀጥልበት የኦነግን አጀንዳ አታራምድ»«የትግራይ ሕዝብ ትልቅ ሕዝብ ነው ፤ ግን እስከመቼ በተወሰኑ ግለሰቦች ሐሳብ እንደሚመራ አይገባኝም»

https://p.dw.com/p/3RXkf
Addis Abeba bannt rechtswidrige Motorräder
ምስል DW/S. Muchie

የማኅበራዉ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

የአማራ ክልል ደህንነት ስጋትና ፀጥታ ምክር ቤት መግለጫ፤ እንዲሁም የህወሃት መግለጫ ሰሞኑን ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በስፋት ያነስዋቸዉ ርዕሰ ጉዳይ ነበሩ። በማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች የተንሸራሸሩ ሃሳቦችን አሰባስበናል። 
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ኖቤል ሽልማት ማግኘት ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ተጠቃሚዉን ሲያነጋገር ሰንብቶአል። በዚህ ሳምንት ደግሞ 'ውሁድ ፓርቲ' ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ግንባሩን ብቻ ሳይሆን አገሪቱንም አደጋ ላይ የሚጥል ነዉ ሲል የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ያወጣዉ መግለጫ፤ በአማራ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት መግለጫ ብሎም የአፋር ነዋሪዎች "መንግስት ጥቃቶችን ያስቁምልን" ሲሉ መጠየቃቸዉ የሰሞንኛ የማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዉ አስተያየት የሰጠባቸዉ ርዕሶች መካከል ዋንኞቹ ነበሩ።
 በያዝነዉ ማክሰኞ አመሻሹ ላይ የህዝባዊ ሓርነት ትግራይ ማእከላይ ኮሚቴ አመሻሹ ላይ ይፋ ያደረገዉን መግለጫ ተከትሎ ህወሀት ከኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ጋር ካለው የአመላከት እና ተግባር ልዩነት አኳያ የውህደቱ አካል ይሆናል ተብሎ እንደማይጠበቅ አብዛኛ የማኅበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች አስተያየታቸዉን አስተላልፈዋል። 
«እኔ እንደሚመስለኝ ከሆነ ያሉት በድሩ ሙዴ የተባሉ የፌስቡል ተከታታይ መግለጫው የትግራይ  ሕዝብን ያልወከለና አንድ እና ሁለት ሰዉ በስሜት የጻፉት ይመስለኛል። ራሱ መግለጫው ኢህአዴግን ብቻ ሳይሆን መላ የኢትዮጵያ ሕዝብን ያሳዘነ ነው።  ተስፋ ያለውን ሕዝብ የሚፈታተን  እና  በጠብ የተሞላ ነው።  በመሆኑም አሁንም ህወሃት ጊዜ አላት ፤ ብትታረም ይሻላታል  እያልኩ የግል አሳቤን ሰጠሁ። ትግራይ ታላቅ ሕዝብ ያለበትና የባለንጹሕ ህሊና ሰዎች መኖሪያና የኢትዮጵያ  ቁንጮ ነች። አንድነትንና የመስማማት መንፈስ ፈጣሪ ይላክልን» ብለዋል። »
« ህወሐት ያወጣው መግለጫ ተስፋ የመቁረጥና አቅጣጫ የጠፋው ዓይነት ሆኖ ነው ያገኘሁት። እንዲያውም የቁም ተዝካሩን ያወጣ ይመስለኛል። ስለዚህ ይቅናው ባይ ነኝ፤ ያሉት ደግሞ አንድነት ታደሰ የተባሉ የፌስ ቡክ ተከታታይ ናቸዉ።»
«እንዳልክ የጆኒ የተባሉ ደግሞ የትግራይ ሕዝብ ትልቅ ሕዝብ ነው ፤ ግን እስከመቼ በተወሰኑ ግለሰቦች ሐሳብ እንደሚመራ አይገባኝም? ትግራይ የሚያስተዳድራት ሰው አላጣችም፤ ግን ምን ዋጋ አለው» ሲሉ ነዉ አስተያየታቸዉን የዘጉት።  «በዶይቼ ቬለ «DW» ፌስ-ቡክ ገጽ ላይ ደግሞ እስቲ ባካችሁ የትግራይን ነገር ለትግራዮች ተዉላቸዉ። ህወሃት ለዘላለም ይኑር» ያሉን ደግሞ ካሊድ ባህሩን ናቸዉ።
«ቅዱ የሰዉሰዉ የተባሉ የፌስ ቡክ ተጠቃሚ ህውሃትን ወክለዉ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ያሉ አመራሮች ከኃላፊነታቸዉ መነሳት አለባቸዉ ምክንያቱም ድርጅታቸዉ ህውሃት ከኢህአዴግ ስላፈነገጠ እንደ ድርጅት መገምገም ወይም በሹመታቸዉ መጠየቅ ስለማይችሉ ከኃላፊነት ቦታዎች ሊነሱ ይገባል።» ብለዋል።   
ደረጀ መንገሻ የተባሉ ደግሞ « ብሔራዊ እርቅ ነው የሚያስፈልገው፣ ያኻላውን እያሰብን የፊታችንን እንዳናበላሽ ወደ እርቅ በአስቸኻይ ቢገባ ጥሩ ነው። ሲሉ መክረዋል» 
ማንም ምንም ቢል ህወሃት የሚለወጠዉ አቋም አይኖርም፡፡ ንፋስ ወደነፈሰ የሚነፍስ ድርጅት አይደለምም።  ይሄንንም ውትፍ ነቃዪ በደንብ ያቀዋል፡፡ ያሉት ደግሞ ሚሊዮን ፀጋዬ ናቸዉ። በማዕከላዊ፣በምዕራብጎንደር፣በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር እና በጎንደር ከተማ «ማንኛውም የኃይል እንቅስቃሴ» በሚያደርጉ አካላት ላይ የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ እንደሚወስዱ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ማስታወቁ ትናንት ሃሙስ በሶሻል ሚዲያዉ ሽፋን ያገኘ ዜና ነዉ።

Das Logo der ADP Amharische Demokratischen Partei
ምስል ADP
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

 
«ዎሌ ይመር እውነተኛ ሰላም ለማምጣት ከሆነ በእውነት የክልሉ ኃይል ከበቂ በላይ ነው። ነገር ግን የሚሰማራው ሁይል ምን ያክል ከዘርና ከብሄር ተንኮል የፀዳ ነው? ይሄን አጋጣሚ በመጠቀም የሚበቀል ሀይል ቢኖርስ? ከዚህ በከፋ መልኩ እኮ ሀገርን ሌት ከቀን የሚያተራምሱትንስ ለምን አንድ አልተባሉም? ኣማራውን በተለየ ኣይን ማየትስ ለምን አስፈለገ ?»
ችግረኛ ቤተሰቦቻችን ወደ ትምህርት ቤት ሂዱ ብሎ ላከን ከንቲባችን ዩንፎርም አልብሶ ፣ የትምህርት ቁሳችን አሟልቶ መግቦ ፤እኩል አርጎ ትምህርት አስጀመረን! መመኪያችን ክፉ አይንካህ! የጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪወች በቦርድ ላይ ከፃፉት! ሲሉ ጽጌ ስላሴ ከበደ በፌስቡክ ገጽ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማን በመምራት ላይ የሚገኙት ታከለ ከሥልጣናቸው ይነሳሉ የሚሉ ዘገባዎች በማኅበራዊ መገናኛዎች ባለፉት ጥቂት ቀናት በሰፊው ከተሰራጨ በኋላና እዉነት ነዉ የሚል ማረጋገጫ ተገኝቶአል የሚል ወሬ ከተሰማ በኋላ የፃፉት ነበር። ። መስርያቤታቸዉ ግን አለ በዚሁ በማኅበራዊ ገናኛ የተሳሳተ መረጃ ነዉ ታከለ ኡማ ስራ ላይ ይገኛሉ ሲል ሃሙስ አመሻሹ ላይ  መረጃዉን አስተላልፎአል።  
ሱሊማን መሃመድ በበኩላቸዉ ኢንጅነሩ መልካም ሰው ብቻ ሳይሆን በርካታ መልካም ስራዎችን እየሰራ ያለ ከንቲባ ነው፡፡ ከኃላፊነት ይነሳል ሲባል ግራ ገብቶኝ ነበር።» ብለዋል
«እውነታው ሌላ ነው! ታከለ ኡማን ለማንሳት ተወስኖ የነበር ቢሆንም ሁለት ቀን በፈጀው የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከፍተኛ ፍጭት ተደርጎ በድምጽ ብልጫ ሳይሳካ ቀርቷ፡፡ ይህንንም የኦዴፓ ስብሰባን መጠናቀቅ ተከትሎ የከንቲባ ጽቤቱ ምክትል ከንቲባው እንደተነሳ የተናፈሰው ወሬ ትክክል አይደለም በማለት ለማስተባበል ተሞክሯል፡፡ ኧረ ለመሆኑ ኢቲቪስ እስከዛሬ ወሬ ሲያደምቅ ቆይቶ ነው አሁን ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ያስተባበለው?! ያሉት ደግሞ አማኑኤል ዘዉዱ ናቸዉ።» 
«ዜድ የተባሉ ደግሞደግሞ ቀጥታ ለታከለ ኡማ የተላከ አስተያየት ይመስላል«  ትንሽ ደንገጥ አድርገህ መመለስህ አይከፋም። በሥልጣን ላይ የመሆንህንና ያለመሆንህን ልዩነቱን ማየት መልካም ነውና። አሁን በደንብ የሚይዝህ ሕዝብ መብዛቱ አይቀርም። የድሆች አባት እግዚአብሔር ይባርክህ። ብዙ ለውጦች በዓይን የሚታዩ ተግባር ያለበትን ሥራ እየሰራህ ነው። ከህዝብ ጋር በአውቶብስ የተሳፈረ መሪ ነህ።» «በየስፍራው ሄደህ ያዘኑ፣ የተጎዱ፣ የተራቡና የተቸገሩን የረዳህ ያጽናናህ ነህ። በታማኝነት አገልግሎትህን ቀጥል። የሰማያዊው ርስት ወራሽ የአባቴ ብሩክ ኢንጂነር ታከለ ኡማ» ብለዋል። ታከለን ስቃወም ነው የቆየሁት አሁን ሊነሳ ነው ሲባል ደብሮኝ ነበር እንኩዋን ተመለስክ በኢትዮጵያዊነትህ ቀጥልበት የኦነግን አጀንዳ አታራምድ፤ ያሉት አብደላ ዩሱፍ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ናቸዉ። ሙሉጌታ አያሌዉ በበኩላቸዉ ታከለ ኡማ ጎጠኛ ነው ብዬ አላስብም ፡፡ እንደ ጠ/ሚ አብይ አገሩን ይወዳል። ነገር ግን እስክንድር ላይ የሚፈጥረው አላስፈላጊ ጫና ይቁም! ብለዋል። 

Das Logo der ADP Amharische Demokratischen Partei
ምስል ADP

ደረጀ ገብረ ኢትዮጵያዊዉ የተባሉ ደግሞ እውነት እውነት እናውራ ከተባለ ታከለ ኡማ ከኃላፊነታቸው አለመነሳታቸው የሚጠቅመው ለአዲስ አበባ ህዝብ ነው። ለእርሳቸው እረፍት ሊሆን ይችላል። እንደ ኢንጅነሩ አይነት መሪ ግን ከ100 ዓመት አንዴ የሚገኝ ይመስለኛል። ኦሮሞ ስለሆናችሁ ታኬ መነሳት የለበትም የምትሉ፤ መነሳት የሌለበት ስለሚሠራ እንጂ ከኦዴፓ ስለመጣ መሆን የለበትም። ብሔራችሁ ከኦሮሞ ውጪ የሆናችሁ ደግሞ ታከለ መነሳት አለበት፤ የአዲስ አበባ ተወላጅ አደለም  ምናምን የምትሉ ሰልጠን ብትሉ ጥሩ ይመስለኛል። የተሠጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ለከተማዋና ለኗሪዎቿ እድገት እስከ ሰራ ድረስ ከጋናም ይምጣ ችግር እንደሌለው ልትረዱ ይገባል። ታከለ ኡማ ኦሮሞን እንዳይከፋው ብሎ አንዳንዴ ደስ ሳይለውም ቢሆን ፊንፊኔ ሲል ስሰማ ትንሽ ቅር ይለኛል። ምክንያቱም ስም እንደ ቋንቋው አይተረጎምም። የአዲስ አበባ ይፋዊ  መጠሪያዋ አዲስ አበባ ነው። ስለዚህ አዲስ አበባ ብሎ የመጥራት ግዴታ አለበት። ስም አይተረጎምም። በተረፈ ሺህ ዓመት ንገስ አቦ ታኬ። ለኔ አንደኛ መሪ ነህ፤መልካም የስራና የጤና የለውጥ ዘመን ይሁንልህ

አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ