የታሰሩ የባልደራስ አመራር ለምርጫ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 17 2013ማስታወቂያ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በቀጣዩ ምርጫ በእጩነት እንዳይቀርቡ ተጥሎባቸው የነበረውን ክልከላ ትናንት ሻረ። ውሳኔው ከሕግ አንፃር ተገቢ ነው ያሉ አንድ የሕግ ጠበቃና አማካሪ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤቱ ብይን አስገዳጅ በመሆኑ የማስፈፀም ግዴታ ይኖርበታል ብለዋል። አመራሮቹ እጩ ሆነው ተመዝግበው፣ በምርጫውም ተወዳድረው ማሸነፍ የሚችሉ ከሆነ የሕግ አፈፃፀሙ ልዩ ልዩ አማራጮች እንደሚኖሩት ገልፀዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ