1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ይዞታ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 4 2011

የኅዳሴው ግድብ እስካሁን ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት እና ሥራውም ለአንድ ቀን እንኳን እንዳልተጓጓተ ከግድቡ ጋር የተዛመዱ የሥራ ኃላፊዎች አስታወቁ። የሥራ ኃላፊዎቹ ይህን ይፋ ያደረጉበት ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የጀመረችውን ታላቁን የኅዳሴ ግድብ የተመለከተ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

https://p.dw.com/p/3A3JV
Äthiopien Podiumsdiskussion zu GERD in Addis Abeba am 13.12.2018
ምስል DW/Y.G.Egziabher

«እስካሁን 98 ቢሊየን ብር ፈጅቷል»

የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ መጠናቀቁን በማመልከትም፤ በሜቴክ ተጓተቱ የተባሉ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን ጨርሶ በሁለት ተርባይን ኤሌክትሪክ የማመንጨት ሥራ ለማስጀመር ሁለት ዓመታት፤ ጠቅላላ ሥራውን ለማጠናቀቅ ደግሞ አራት ዓመታት እንደሚፈጅ ተነግሯል። ወኪላችን ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል።

 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ