የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ውዝግብ
የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳንን የሚያወዛግበውን የሕዳሴው ግድብ ውዝግብ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የመፍታት ሠፊ ዕድል እንዳለው ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የውሃ ልማት ምሁራን ገለፁ:: ምሁራኑ እንደሚሉት በሦስቱ ሃገሮች መኻከል በጎ ፈቃደኝነቱ ካለ ህብረቱ ውዝግቡን መዳኘትና መፍታት ይችላል:: ኢትዮጵያ ከወዲሁ ዲኘሎማሲያዊ ዘመቻዋን አጠናክራ ማካሄድ እንዳለባትም አስገንዝበዋል::
ታሪኩ ኃይሉ