1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የ«ታላቁ ሕዳሴ ግድብ» ውኃ ሙሌት 

ዓርብ፣ ግንቦት 20 2013

አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ ዕቀባ ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌትም ሆነ ከአጠቃላይ የግድቡ ግንባታ ተለይቶ መታየት ያለበት መሆኑን የውኃ ተመራማሪው ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ለ ዶይቼ ቬለ ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/3u44k
Äthiopien Grand-Ethiopian-Renaissance-Talsperre
ምስል AFP/Maxar Tech

የውኃ ሙሌቱ ቀድሞም ጀምሯል የሚሉ አሉ

አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ ዕቀባ ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌትም ሆነ ከአጠቃላይ የግድቡ ግንባታ ተለይቶ መታየት ያለበት መሆኑን የውኃ ተመራማሪው ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ለ ዶይቼ ቬለ ተናገሩ። መንግሥት አሜሪካ እዚህ ውስጥ ምን ያገባችኋል ሊባሉ ይችላሉ ሲል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ገልጿል። ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ግብፅ ከአሜሪካ ያላት ቅርበት ኢትዮጵያን ለመጉዳትና ለማሻሻጥ እንዲሆን ማንም አይፈቅድም ብለዋል። መንግስት የግድቡ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚከናወን ደጋግሞ አሳውቋል። ሆኖም መረጃዎች የሚጠቁሙት መንግሥት የውኃ ሙሌቱን በዚህ ወር አስቀድሞ መጀመሩን ነው። 

ሰለሞን ሙጬ 
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ