1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ውዝግብ

እሑድ፣ ጥር 10 2012

በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ያካሄዱት ውይይት በመግባባት መጠናቀቁን ሦስቱ ሃገራትና ታዛቢዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።በዚህ ውይይት ሦስቱም ወገኖች በግድቡ ውኃ ሙሌት እና የሥራ አካሄድ ላይ አጠቃላይ፣ አግባቢ ተግባራዊ የሚሆን ዘላቂ እና የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ ከተባለ ስምምነት ላይ ለመድረስ ቃል መግባታቸውም ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/3WPoB
Grand Ethiopian Renaissance Dam
ምስል picture-alliance/dpa/G. Forster

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ውዝግብና መፍትሄዎቹ

ኢትዮጵያ ከግዛቷ የሚነሳውን የአባይን ውኃ ለኃይል ማመንጫነት ለመጠቀም በጀመረችው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ሥጋት ካሳደረባቸው ከሱዳን እና ግብጽ ጋር የምታደርገው ውይይት እንደቀጠለ ነው። ሦስቱ ሃገራት ሲያካሂዱ የቆዩት ንግግር አሜሪካን እና የዓለም ባንክንም በታዛቢነት ከጨመረ ወዲህ ዓለም ዓቀፍ ትኩረት ስቧል።ከዚያን ወዲህ በጉዳዩ ላይ በውኃ ሚኒስትሮች ደረጃ በካይሮ በካርቱም እና በአዲስ አበባ የተካሄዱት 4 ንግግሮች ያለ ስምምነት ነበር የተጠናቀቁት።የሦስቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ እና የውኃ ሚኒስትሮች በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ያካሄዱት ውይይት ግን በመግባባት መጠናቀቁን ሦስቱ ሃገራትና ታዛቢዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።በዚህ ውይይት ሦስቱም ወገኖች በግድቡ ውኃ ሙሌት እና የሥራ አካሄድ (Operation) ላይ አጠቃላይ፣ አግባቢ ተግባራዊ የሚሆን ዘላቂ እና የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ ከተባለ ስምምነት ላይ ለመድረስ  ቃል መግባታቸውም ተገልጿል።በዚሁ መሠረት በመጨረሻው ስምምነት ላይ ተወያይተው ለማጽደቅ ጥር 18 እና ጥር 19 2012 ዓም ዋሽንግተን ውስጥ እንደገና ለመሰብሰብ መስማማታቸውም በመግለጫው ተጠቅሷል።የዛሬው እንወያይ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አወዛጋቢ ጉዳዮች እና መፍትሄያቸው ላይ ያተኩራል በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል።ዶክርተር ያዕቆብ አርሳኖ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሣይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምሕር እና የውኃ ፖለቲካ(የኃይድሮ ፖለቲክስ ተመራማሪ ዶክተር ሰሙ ሞገስ በዩናይትድ ስቴትስ ከኔቲከት ዩኒቨርስቲ adjunct ፕሮፌሰር ወይም ተባባሪ መምህር የውሐ መሀንዲስና አጠቃቀም ምሁር እና አማካሪ እንዲሁም ዶክተር ጌታቸው በጋሻው በአሜሪካን ቺካጎ ሀፐር ኮሌጅ የኤኮኖሚ መምህር ናቸው።ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምፅ ማዕቀፍ ይጫኑ

ኂሩት መለሰ