1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታህሳስ 15፣2011 ዓም የስፖርት ዝግጅት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 15 2011

በሴቶች አትሌት ፀሐይነሽ ሳለ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ከ36 ሴኮኖድ በአንደኝነት ጨርሳለች። በወንዶችም አትሌት ማዘንጊያ አያሌው ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ከ47 ሴኮንድ ነበር በአንደኝነት የፈጸመው።

https://p.dw.com/p/3AbK7
Frankreich junger äthiopischer Fußballverein in Paris
ምስል Haimanot Tiruneh

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በደቡብ ቻይናው የሃይነን ጃን ዶ ማራቶን በወንዶችም በሴቶችም ድል ተቀዳጅተዋል። በሴቶች አትሌት ፀሐይነሽ ሳለ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ከ36 ሴኮኖድ በአንደኝነት ጨርሳለች። በወንዶችም አትሌት ማዘንጊያ አያሌው ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ24 ደቂቃ ከ47 ሴኮንድ ነበር በአንደኝነት የፈጸመው።ቤቻ ደረጀ ኡርጌቻም ውድድሩን በ3ተኝነት ጨርሷል። የኢትዮፕያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያዘጋጀው ዓመታዊ የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር የመካከለኛ የእርምጃ እና የሜዳ ተግባራት የአትሌቲክስ ሻምፕዮና ነገ ታህሳስ 16፣2011 በአዲስ አበባ ስታድዮም እንደሚጀመር የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል። እስከ ፊታችን እሁድ ስለሚቀጥለው ስለዚሁ ውድድር ዓላማና ይዘት DW የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያን አነጋግሯል። እግርኳስም በስፖርት ዝግጅት ተካቷል። አዘጋጅዋ ሃይማኖት ጥሩነህ ታቀርብልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ