1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐሙስ ነሐሴ 14 ቀን 2013 ዓም የማኅበራዊ ዘዴዎች ቅኝት

ዓርብ፣ ነሐሴ 14 2013

«ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን የሚያከብሩትን ሃገራት እናከብራለን፤ሃገራችንን የማያከብሩትንና የሚያሸማቅቁትን ግን ለማክበር እንቸገራለን።»

https://p.dw.com/p/3zI06
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed
ምስል Tiksa Negeri/REUTERS

የነሐሴ 14 ቀን 2013 ዓም የማኅበራዊ ዘዴዎች ቅኝት

የዛሬው የማኅበራዊ ዘዴዎች ቅኝት ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አነጋጋሪ በነበሩ ሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።ኂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች። 
በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተለያዩ ሃሳቦች ከተንሸራሸሩባቸው ጉዳዮች መካከል የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዚህ ሳምንት የቱርክ ጉብኝትና ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የሚባረሩ ዜጎች ጉዳይ ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዚህ ሳምንት በአንካራ ቱርክ ያደረጉት የአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት ከቱርክ ጋር አራት ስምምነቶች በመፈራረም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ትናንት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። የሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት 125 ዓመት በሞላበት በዚህ ወቅት ላይ ሁለቱ ሃገራት «በውሀ ዘርፍ ትብብር ለማድረግ የጋራ መግባቢያ ሰነድ፣ የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት፣ የፋይናንስ ድጋፍን የተመለከተ የትግበራ ሰነድ እና የወታደራዊ ፋይናንስ የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን ነው ጽህፈት ቤቱ ያስታወቀው ።ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማካሄዳቸውን፣በውይይቱም ወደፊት ትብብራቸውን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውንም አትቷል። 
ከትናንት ወዲያ በተፈረመው የቱርክና የኢትዮጵያ ስምምነት ላይ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሉዩ ልዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።አስናቀ አስናቀ መርጋ « እጅግ በጣም ምርጥ ውብና ማራኪ ዲፕሎማሲ ነው።በተፈተንበት በዚ ወቅት ከጎናችን ለተገኙ ጓዶች እኛ ኢትዮጵያውያን ክብር እንሠጣለን እናመሠግናለን ብለዋል። መሃሪ በላቸው «ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን የሚያከብሩትን ሃገራት እናከብራለን፤ሃገራችንን የማያከብሩትንና የሚያሸማቅቁትን ግን ለማክበር እንቸገራለን።» የሚለውን አስተያየት በፌስቡክ አስፍረዋል።ቢንያም ጌታቸው ደግሞ «ሁሌም እውነት አሸናፊ ናት ዛሬ ጥሩ ላይመስል ይችላል ግን ነገ ኢትዮጵያ ከሀያላን አገራት ትርታ እንደምትሰለፍ ያሳየ ስምምነት ነው ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ድል ለሰፊው ህዝብ በማለት ሃሳባቸውን አጠቃለዋል። 
 እናመሠግናለን ቱርክ የኢትዮጵያን መሪ ስታከብር ኢትዮጵያን አከበረች ይህ ደግሞ የክንፈ ገብረ እግዚአብሔር ምስጋና ነው። 
 
 «ዐቢይ ከታላቋ ሀገረ መሪ ጋር ስምምነት ሲያደርግ የህወሓት አመራሮች ደግሞ ከኦነግ ሸኔ ጋረ ይድራደራሉ ቀን የጣለው ማለት ይህ ነውና ።=የሚለው ደግሞ ሀብታም ጌታሁን ነው። 
በቅድምያ እግ/ር ይመስጌን 
ዶ/ር አብይን እግ/ር ይጠብቅልን።የቱርክን ህዝብና መንግስት እንድሁም ፕረዝደንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻንን እጅግ በጣም እናመሠግናለን።ጠላቶቻችን ከዝህ ብዙ ይማራሉ ብዬ አምናለሁ።ያሉት ደግሞ ግርማ ዲጋኖ ናቸው። አይናለም ታደሰ ዳዳ በሚል የፌስቡክ ስም የሰፈረ ሃሳብ ደግሞ «ቸግሯችኋል ማለት ነው። በመጨረሻው ደቂቃ ከኤርዶጋን» ይላል 
ሔኖክ ሰማኝ 
አሁን ኢትዮጵያ በትክክለኛዉ የባቡር መስመር ዉስጥ ገብታለች።ጠላቶቿ በሙሉ በየ መንገዱ እየተጠባጠቡ ያልቃሉ።ኢትዮጵያን ከጉዞዋ የሚያስቆማት የለም ብለዋል። 
 
ራብያት ሃሰን መፍትሄ የሚሉትን ነው የጻፉት  
 «በዚህም ተባለ በዛ ሲሉ የጀመሩት ራብያት ያለው ትልቁ መፍትሄ ወደሰላም መሄድ ብቻነው 
የሰላም ድርድር እንደ ጦርነት አዋጅ ቀላል እንዳልሆነ ግልፅነው ። 
ክብደቱ የሚቀንሰው ግን ከልብና በሃቅ በመስራት ነው ። ሲሉ ደምድመዋል።
ሄኖክ ጌታቸው በአፍሪካ ቀንድ ላይ የጦር ሠፈር ከገነቡ አገሮች የቱርክ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለየት ይላል ሩቅ ምስራቅ እንዳሉት ዘላቂ ጥቅም እንጂ ዘላቂ ወዳጅ የለም የሚሉት ሃይነት አይደለም የኛ ወዳጅነት በልብ እንጂ በኪስ አይያዝም ... በማለት አስተያየታቸውን አስፍረዋል።
ደነቀ ማሞ  «የኢትዮጵያን ጠላት ያጥፋልን ፣የኢትዮጵያን ወዳጃችንን ያብዛልን ካሉ በኋላ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወታደር መሆናቸውንም ገልጸዋል።
 
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት «ሕገ -ወጥ» የሚላቸውን በየእስር ቤቶቹ የጎራቸውን  ተጨማሪ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደ ሐገራቸዉ መላኩን በዚህ ሳምንትም ቀጥሏል። ።የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን በጅምላ መያዝና ማሰር ከጀመረበት ካለፈዉ ሐምሌ ጀምሮ በሶስት ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ከ40 ሺሕ የሚበልጡ ኢትዮጵያዉያንን ወደ ሐገራቸዉ ልኳል።በጂዳ የኢትዮጵያ ቆስላ ምክትል ኃላፊ ነብዩ ተድላ በተለያዩ የሳዑዲ አረብያ እስር ቤቶች የተያዙ ኢትዮጵያውያን ከትናንት አንስቶ ወደ ሃገራቸው እየተላኩ መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። በጥቅሉ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ያሏቸው ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሳዑዲ አረብያ ማቆያዎች አሁንም እንደሚገኙ ነው ነብዩ ለዶቼቬለ የተናገሩት።  
በዚህ ጉዳይ ላይ በዶቼቬለ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።አሌክስ ሎግ አውት በሚል የፌስቡክ ስም   
 የሰፈረ አስተያየት «እግዚሐብሄር ቀን አለው!እነሱም እንደዚህ የሚሆኑበት ቀን ሩቅ አይደለም።።የደሀ እምባ ፈሶ አይቀርም» ይላል  እያሱ አደናም ተመሳሳይ አስተያየት ሰጥተዋል፤«የጊዜ እንጅ የሰው ጀግና የለም እጃችን ላይ ትወድቃላችሁ ግፋችሁ በዝቶልና ኢትዮጵያ ቀን ይወጣላታል ያውም አሁን በቅርብ»ሲሉ  
 «ለአረቦች ኢትዮጵያ የስደት ጊዜ ማረፊያ ጎጆ ነበረች በነብዩ መሐመድ ዘመን።ነብዩ መሐመድም "ኢትዮጵያውያንን አትንኩት" ብለዋቸው ነበር።ዛሬ ግን አረቦች ኢትዮጵያውያንን በባዶ እግር ወደ አገራቸው መሸኘታቸው በጣም ያመናል።ይህም ያልፋል የማያልፍ የለምና» ብለዋል ሚኪያስ በየነ ።መብራቱ ኪዳን ደግሞ በሰላም መሸኘታቸው በራሱ ያመሰግናቸዋል ብለዋል።ሳምሶን አብርሃም  ቁጭት የተሞላበት አስተያየት ነው የሰጡት።«ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረትና ላብ መለወጧ አይቀርም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ይሄን አለም ያየዋል»በማለት  
  
በጂዳ የኢትዮጵያ ቆስላ ምክትል ኃላፊ ነብዩ ተድላ ለዶቸ ቬለ እንደተናገሩት የኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባደረጉት ስምምነት መሠረት በየሳምንቱ ሶስቴ በሚደረግ በረራ በሳምንት አንድ ሺሕ ኢትዮጵያዉያን ሐገራቸዉ ይገባሉ።ስደተኞቹን ወደ ሐገራቸዉ መመለሱ ትናንት ከሪያድ ሳዑዲ አረቢያ ተጀምሯል። 
 አቡሸገር ስደተኛው «በሳምንት 1000 በጣም ፌዝ ነው እስር ቤት ውስጥ ከስልሳ ሺህ በላይ ታጉሯል በየቤቱ ትኬት ቆርጦ ለመውጣት የተዘጋጀው ቤት ይቁጥረው እንደገናም በየመንገዱ ሀበሻውን እያሯሯጡ መያዙን አላቆሙም ነገሩ ሁሉ ውሃ ቢወቅጡት አንቦጭ ነው ማለት ይቀላል ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል። 
የሳዑዲ አረቢያ ፀጥታ አስከባሪዎች መኖሪያ ቤቶችን ጭምር እየሰበሩ ኢትዮጵያዉያንን በጅምላ የመያዝ ዘመቻ በመጠኑም ቢሆን መቀነሱ ተዘግቧል።  በጂዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ምክትል ሃላፊ አቶ ነብዩ ተድላ እንዳሉት ደግሞ  ፀጥታ አስከባሪዎች መኖሪያ ፍቃድ ያላቸዉ ኢትዮጵያዉያንን መያዛቸዉንም፣ ካሰሩ በኋላ አሻራ እያነሱ መልቀቃቸዉን ቀንሷል። ሁለት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ግን ይህ ትክክል አይደለም ሲሉ ጽፈዋል አለሙ ጀማል አንዱ ናቸው። «በሳምንት1000 ማለት እያቀለዱ መሆን አለበት! ቤት ሰበራው እና አፍሰውስ የት ነው የቀነሳው? ሲሉ ጠይቀዋል። ሰይድ ተማም «አፈሳውም ሆነ ቤት ሰበራው አልቆመም dw እያጣራቹ ለምን አትዘግቡም ሲሉ እኛንም ወቅሰዋል። ሰይድ ተማም ዶቼቬለ አፈሳውም ሆነ ቤት ሰበራው ቀነሰ እንጂ ቆሟል አላለም፤ልብ ይበሉ።ምስክር ሙሉቀን «ስደት የተጀመረዉ ምናልባት ከሳዉዲ ወደ ኢትዮጵያ ይመስለኛል ለማነኛውም ታሪክ ይቀየራል» ሲሉ።
ዮናታን ይመኑ «እንደው ሳውዲ መጨረሻሽን ያሳየን በእውነት ቅሌትሽ ቅጥ አጣ በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
ኂሩት እሸቱ ደግሞ የኢትዮጵያውያኑን ከሳዑዲ መባረር በበጎ ነው ያዩት «ጌታ ሆይ አንድ ላይ እየሰበሰብከን ነውና በምክንያት ፣እናመሰግንሀለን በሰላም ኑልን ተርበንም ተጠምተንም በአንድ ላይ ክፉ ቀንን ያሳልፍልናል እንፀልይ አብዝተን»ብለዋል። 

Illegale aus Äthiopien in Saudi-Arabien
ምስል DW/Sileshi Sibiru

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ